1. ዓላማዎች
የሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በማቋቋሚያ አዋጁ አንቀጽ 4 መሠረት ሶስት ዋና ዋኛ ዓላማዎች አሉት፡፡ እነዚህም ዓላማዎች፡-
-
በፌደራሉና በክልሉ ሕገ መንግሥት እንዲሁም በሌሎች አግባብነት ባላቸው ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነትን ማበረታታት፡፡
-
የክልሉ ነዋሪ ለመረጃ ቅርበት እንዲኖረው ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን እንዲያገኝ ማድረግ፤ በዚህም በዋና ዋና የሀገሪቱና የክልሉ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር እንዲችል መስራት፡፡
-
በክልሉ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ አጋዥ ሚና መጫወትና በሕብረተሰቡ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ባሕል እንዲጎለብት ማበረታታት፡፡
2. ተልዕኮ (Mission)
ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነትን በማበረታታት፣ የክልሉ ነዋሪ ለመረጃ ቅርበት እንዲኖረው በማድረግ፣ በዋና ዋና የሀገሪቱና የክልሉ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባትን በመፍጠር፣ በክልሉ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ አጋዥ ሚና መጫወትና በሕብረተሰቡ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ባሕል እንዲጎለብት ማበረታታት።
3. ራዕይ (Vision)
በ2030 በሀገሪቱ ከሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ተወዳዳሪና ተመራጭ ሚዲያ ሆኖ መገኘት።
4. እሴቶች (Values)
- የተገባ እና ትክክለኛ አገልግሎት ለመስጠት (Professionalism & continuity)
- ለጊዜ ዋጋ መስጠት
- እያዝናኑ ማስተማር
- ወጪ ቆጣቢነት
- መልካም ስብዕና
- ተከታታይነት ያለው መሻሻል
- የለውጥ ሐዋሪያ መሆን
- ጥበባዊ ፈጠራ
- ሙያዊ ስነምግባር