728 ሺህ ቶን የወተት ምርት ወደ ገበያ መቅረቡን የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ገለፀ።

728 ሺህ ቶን የወተት ምርት ወደ ገበያ መቅረቡን የሲዳማ ክልል  እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ገለፀ።
ሀዋሳ:-ሐምሌ 30/2018ዓ/ም (ኤስ ቢ ሲ)
728 ሺህ ቶን የወተት ምርት ወደ ገበያ መቅረቡን የሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ፎና ገልጸዋል።
ኃላፊዉ ይህንን ያሉት የቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ሥራ አፈፃጸም እና የ2019 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ግምገማ መድረክ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነዉ።
መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፌ ጉባዔ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ ዛሬ እዉቅና የተሠጣቸው አካላት ለሎች ምሳሌ እንድሆኑና ለነገ ሥራቸው እንዲነሳሱ ያደርጋቸዋል ነዉ ያሉት።
ዘርፋን ውጤታማ ለማድረግ በእንስሳት መኖና ጤና ላይ እየተሠራ ያለዉ ሥራ አበረታች ነዉ ያሉት አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ አሁን በዚህ ዘርፍ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።
በጠንካራ ተቋም ለመፍጠር የዓመቱን ዕቅድ በአግባቡ መፈፀም አስፈላጊ መሆኑን ያነሱት አቶ አሰፋ ፎና የማሕበረሰቡን ሕይወት ለመቀየረ በሌማት ትሩፋት ላይ እየተሠራ ያለዉ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ ጥሩ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ባለሙያዎች ላይ እዉቅና ተሰጥቷቸዋል ።
በታመነ አረጋ
ለሃሳብ ልዕልና
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ