የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተቋማትን የማስፈፀም አቅም ለማጎልበት የተገዙ ልዩ ልዩ ማሽኔሪዎችና የቢሮ ተሽከርካሪዎች የርክክብ ስነ ስርዓት አካሄደ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተቋማትን የማስፈፀም አቅም ለማጎልበት የተገዙ ልዩ ልዩ ማሽኔሪዎችና የቢሮ ተሽከርካሪዎች የርክክብ ስነ ስርዓት አካሄደ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተቋማትን የማስፈፀም አቅም ለማጎልበት የተገዙ ልዩ ልዩ ማሽኔሪዎችና የቢሮ ተሽከርካሪዎች የርክክብ ስነ ስርዓት አካሄደ።

********


በርክክብ መድረክ ላይ የተገኙት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍና የተገልጋይን እርካታ ከፍ ለማድረግ የሚረዱ የተለያዩ ማሽኖችን ወደ 263 ሚሊዮን ብር ወጪ በማውጣት መገዛቱን ገልፀው፤ የተገዙ ማሽኖች የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ የሚያግዙና የተጀመሩትን ፕሮጀክቶች የሚያፋጥኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።


ከዚህ ቀደም ስራዎች በኪራይ ይሰሩ እንደነበረ የጠቀሱት ከንቲባው አሁን በራስ አቅም የተገዙ እነዚህ ማሽነሪዎች ለከተማው ፅዳትና ውበትን ለመጠበቅ ብሎም ለቆሻሻ አወጋገድ ወሳኝ ፋይዳ ያላቸው መሆናቸውን ጠቅሶ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እነዚህ ማሽኖች እንዲገዙ በማስተባበር የበኩላቸውን የተወጡ አካላትን አመስግነዋል።


 የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ገዳሁን ጋቢሶ እንደገለፁት በተያዘው በጀት አመት ለከተማው ውበት የሚረዱና የተሰሩ የልማት ስራዎችን የሚያቀላጥፉ የመሰረተ ልማት ማሽነሪዎች ዶዘር፣ ትራክተር፣ባክ ሎደርና ኤክስካቫተሮች የተሰሩ የከተማው የውበት ስራዎች ተውበው እንዲቀጥሉ ለማድረግ የተገዙ የቆሻሻ ማስወገጃ ማሽኖች መሆናቸውን ጠቅሰው፤8 ታዳሽ ሃይልን ታሳቢ ያደረጉ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎችና ሁለት የፕሮቶኮል መኪናዎች በድምሩ 10 መኪኖች መገዛታቸውንም ገልፀዋል።


እነዚህ የተገዙ ማሽነሪዎችና የቢሮ አገልግሎት ማሳለጫ መኪኖች በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የተለያዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን እንዲሁም የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ከማፋጠን አንፃርና ቀድሞ የተሰሩት ውበታቸውን ጠብቆ እንዲቆዩ ለማድረግ ያላቸው ሚና ቀላል እንደልሆነም ነው የተገለጸው።


በሚካኤል ኡጋሞ



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ