የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የትምህርት ንቅናቄ መድረክ  ከባለድርሻ አካላት  ጋር አካሄደ ።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ ።
************
ሀዋሳ፣ ነሐሴ 13/2018 ዓ/ም (ኤስቢሲ)
የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ማሻሻል፣ የትምህርት ጥራትን ማሳደግና የትምህርት ተቋማትን አቅም ማጠናከር በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውም ተገልጿል።
በመድረኩ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ብርሃኑ ደሳለኝ እንዳሉት የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግ የትምህርት ቤቶች ማስፋፊያና ጥገና፣ የመማሪያ ክፍሎችን ምቹ ማድረግ፣ የተማሪዎች ምገባና የመምህራን ስልጠና በትኩረት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መሆናቸውን አንስተዋል ።
የመምህራንን አቅም ለማሳደግ ስልጠና ከመስጠት ባለፈ ቴክኖሎጂን በትምህርት ሂደት ውስጥ ማስፋፋት ላይም ትኩረት መደረጉን ጠቁመዋል ።
የበጀት ግልጽነትና የሀብት አጠቃቀም፣ ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም ማጠናከር እንዲሁም የግል ትምህርት ቤቶችን ወደ ተፈላጊው ደረጃ ማምጣትም በትኩረት እየተሰራበት መሆኑን ተናግረዋል ።
የትምህርት ዘርፉ ካሉት ተግዳሮቶች መካከል ሞዴል ትምህርት ቤቶችን በተፈላጊው ደረጃ ማሳደግ አለመቻል፣ የቴክኖሎጂና የአስተሳሰብ ክፍተት፣ ግብዓትን በአግባቡ አለመጠቀም፣ የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር በሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመሆንና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ውስን መሆን ኃላፊው ጠቅሰዋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ማራዶና ዘለቀ በበኩላቸው
የትምህርት ጉዳይ የሁሉንም ወገን ተሳትፎ የሚፈልግ በመሆኑ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በተለይም የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ጥራትን ማሻሻል፣ የተጀመሩ የትምህርት ቤት ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅና በሁሉም ትምህርት ቤቶች የተመጣጠነ የትምህርት ውጤት ማምጣት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን አስረድተዋል።
አቶ ማራዶና አክለውም በ2018 ዓ.ም ከቀደመው የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው፣ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ይበልጥ ለማሻሻል ከመምህራንና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በመመካከር እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰሩ፣ ያሉ ሀብቶችን በአግባቡ እንደሚጠቀሙና ሁሉም ባለድርሻ አካላት በመናበብ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።
በቀጣዩ የትምህርት ዘመን የአመራሩን ቁርጠኝነትና ትኩረት ማጠናከር፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራርን ማስፋፋት፣ የተማሪዎችን ምገባ ማጠናከር እና የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ወደተሻለ ደረጃ ማድረስ ቁልፍ ተግባራት እንደሚሆኑ በመድረኩ ተጠቁሟል።
በ ቆንጅት አየለ
ለሃሳብ ልዕልና
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ