ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ጎበኙ

አጀንዳዎችን ሲያጣጥሙ የነበሩ ተወካዮች ለስራ ቡድናቸው አቀረቡ

********


ሀዋሳ፣ ነሐሴ 11፣ 2018 (ኤስቢሲ)


ከስምንቱ የሥራ ቡድኖች የተውጣጡ 15 የአጀንዳ ምክረ-ሃሳብ አጠናቃሪዎች ያጠናቀሩትን የአጀንዳ ሃሳብ ለየስራ ቡድናቸው አቅርበዋል።


500 አባላት ካሏቸው ስምንት የስራ ቡድኖች ከእያንዳንዳቸው 15፣ በድምሩ 120 አባላት ያሉት ቡድን ካለፈው ሐሙስ ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የሥራ ቡድኖች የተነሱ የአጀንዳ ምክረ-ሃሳቦችን በማዳመጥ ወጥ የሆነ ምክረ-ሃሳብ ማቅረብ የሚያስችል ሥራ ሲሰራ ቆይቷል።


የእያንዳንዱ የሥራ ቡድን ተወካዮችም የየቡድናቸውን የአጀንዳ ምክረ-ሃሳቦች ድግግሞሽ በማስወገድ፣ ያልተቀናጁ ሀሳቦችን በማደራጀት ወጥ የሆነ ሰነድ አዘጋጅተው ዛሬ ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 500 አባላት ላሉት የሥራ ቡድን አቅርበዋል።


የተደራጁ አጀንዳዎች የቀረቡላቸው ስምንቱ የሥራ ቡድኖች ሃሳብ እና አስተያየት አክለው የመጨረሻው ሰነድ እንዲዘጋጅ ለአደራጅ ቡድኖቹ መልሰዋል።


ግብአቶችን የሰበሰቡ የአጀንዳ ምክረ-ሃሳቦችን የሚያጣጥሙ ቡድኖችም የተሰጧቸውን ሃሳቦች በነገው ጠዋት መርሃ-ግብር አካተው ለየሥራ ቡድኖቻቸው በከሰዓቱ መርሃ-ግብር በድጋሚ በማቅረብ እንደሚያፀድቁ ይጠበቃል።



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ