በኦሊምፒክ መድረክ ማሸነፍ ትልቁ ሕልሜ ነው-አትሌት አልማዝ ዮሐንስ

በኦሊምፒክ መድረክ ማሸነፍ ትልቁ ሕልሜ ነው-አትሌት አልማዝ ዮሐንስ
በኦሊምፒክ መድረክ ማሸነፍ ትልቁ ሕልሜ ነው-አትሌት አልማዝ ዮሐንስ
*********
ሀዋሳ፣ ነሀሴ 10፣ 2018 (ኤስቢሲ) በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ለኢትዮጵያ ወርቅ ላስገኘችው ለአትሌት አልማዝ ዮሐንስ በ«ዳኤ ቡሹ» ባህላዊ ሥነሥርዓት በአዲስ አበባ የሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆች አቀባበልና የሽልማት መርሐግብር አካሄዱ።
አትሌቷ በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና በ3000 ሜትር መሰናክል የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል።
አትሌት አልማዝ ዮሐንስ እንደ አትሌት በላይነህ ዴንሳሞና አትሌት ሳሙኤል ፍሬው ከሲዳማ ክልል የወጣች ድንቅ አትሌት ናት። በአትሌቲክስ ሕይወቷ አቅሟን አይቶ ለዚህ ስኬት ላደረሳት አሰልጣኝ ሳሙኤል በቀለን አመስግናለች።
በቀጣይ የአትሌቲክስ ሕይወቷ በኦሊምፒክ መድረክ ማሸነፍ ትልቁ ሕልሟ መሆኑን ገልጻለች።
በዚህ የምስጋና መርሐግብር ላይ አትሌት በላይነህ ዴንሳሞ፣ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርን ጨምሮ የሲዳማ ኮሙዩኒቲ ማኅበርና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ