የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በወተት ላሞች አያያዝና በወተት ልማት ዙሪያ ለሲዳማ ክልል ልማት ሰራተኞች ለ 3ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየሰጠ ነው።

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በወተት ላሞች አያያዝና በወተት ልማት ዙሪያ ለሲዳማ ክልል ልማት ሰራተኞች ለ 3ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየሰጠ ነው።

ሀዋሳ:-ሐምሌ30/2018 ዓ/ም(ኤስ ቢ ሲ)


የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ታፈሰ ማቲዎስ ስልጠናው ዩኒቨርሲቲው ለህብረተሰቡ የሚያደርገውን የአገልግሎትና የዕውቀት ሽግግር በተግባር ያሳየበት መሆኑን ገልጸፀዋል። 


ዶክተር ታፈሰ ማቲዎስ ባደረጉት ንግግር ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ-ገዝ ምርምር ዩኒቨርሲቲ እየተሸጋገረ ባለበት በዚህ ወቅት በምርምር የተገኙ ሳይንሳዊ ዕውቀቶችንና ቴክኖሎጂዎችን በቀጥታ ወደ ህብረተሰቡ ማውረድና የህዝብን ኑሮ መለወጥ ዋነኛ ግቡ መሆኑን አስገንዝበዋል። የሲዳማ ክልል በወተት ሃብት ልማት ረገድ ትልቅ አቅም ያለው ቢሆንም የአመጋገብ ስልት፣ የበሽታ መከላከል እና የዘመናዊ አያያዝ ክፍተቶች የወተት ምርታማነቱን ማነቆ ሆኖ መቆየታቸውንም ጠቅሰው ከ ዛሬ ጀምሮ ለ 3ቀናት በሚደረገው ስልጠና መሰል ክፍተቶችን በመድፈን ከክልል አልፎ በ ሀገር ደረጃ ምርታማነት ከፍ ለማድረግ የሚኖረው አስተዋፆ ከፍ ያለ እንደ ሆነ ገልፀዋል። 


 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የእንስሳት ትምህርት ክፍል ሀላፊና ተመራማሪ ዶ/ር ስንታየው ይግረም የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ለ ተከታታይ 3 ቀናት በሚደረገው ስልጠና ሰልጣኞች ያገኙትን ዘመናዊና ሳይንሳዊ የወተት ላሞች አያያዝ ዕውቀት ወደየአካባቢያቸው ሲመለሱ በተግባር ላይ ማዋል እንዳለባቸው ገልፀው ይህም ንጹህና ጥራት ያለው ወተት በማምረት የክልሉን የስነ-ምግብ ዋስትና ያረጋግጣል በማለት ዩኒቨርሲቲው መሰል ተግባራዊ ስልጠናዎችንና የሙያ እገዛዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል።


የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር ማርቆስ ፍሰሀ በበኩላቸው በክልሉ የወተት ምርታማነት አነስተኛ ሆኖ የመቆየቱ ዋና ምክንያት የወተት ላሞች አመጋገብ ባህላዊ መሆን፣ የምጥን መኖ እጥረት እና የላሞች አያያዝ ዘመናዊ ሳይንሳዊ እውቀትን የተከተለ ባለመሆኑ ነው። ዩኒቨርሲቲያችን ያደረገው ይህ የምርምርና የክህሎት ሽግግር የልማት ሰራተኞች በቀጥታ ወደ አምራቹ በመሄድ እነዚህን ተግዳሮቶች በተግባር እንዲፈቱ ያግዛቸዋል። ይህንን እውቀት ወደ ታችኛው አርሶ አደር በማውረድ ዘርፉን ለማጠናከርና ምርታማነትን ከፍ በማድረግ ረገድ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ይስራል ብለዋል።


ናርዶስ አየለ


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB1o



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ