የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግሥት አገልግሎቶች ዜጎችን ያለአላስፈላጊ እንግልት፣ መዘግየትና ተጨማሪ ወጪ በፍጥነትና በቀላሉ እንዲደርሱ እያደረገ መሆኑን ሲዳማ መሶብ አንድ ማዕከል ገለጸ።
***********
ሀዋሳ፣ ነሐሴ 16/2018 ዓ/ም (ኤስቢሲ)
በልዩ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር ለሲዳማ መሶብ አንድ ማዕከል ሠራተኞችና አመራሮች በተዘጋጀው የአገልግሎትና የሥራ ማነቃቂያ ስልጠና ሰቷል።
የሲዳማ ክልል ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ቢሮ ኃላፊ አቶ መንግሥቱ ማቲዎስ ፣ የመሶብ አንድ ማዕከል ዋና ዓላማ ዜጎች ከእንግልት ነፃ የሆነ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ግልጽ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል መሆኑን ገልጸዉ
በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት ዜጎች እጅ መንሻ እንዳይጠየቁ የሚገባቸውን አገልግሎት በጊዜውና በተገቢው መልኩ እንዲያገኙ መሶቡ እገዛ እያደረገ ነዉ ብለዋል።
በሲዳማ መሶብ አንድ ማዕከል ከ100 ሺህ በላይ ተገልጋዮች አገልግሎት ማግኘታቸውን የገለጹት አቶ መንግሥቱ፣ አገልግሎቱን በክልሉ በስድስት ከተማ አስተዳደሮች የማስፋት ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የሲዳማ መሶብ አንድ ማዕከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንግዳየሁ ዘውዴ በበኩላቸው፣ በ2017 ዓ.ም. ተግባራዊ የሆነው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግሥት አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ የሚያግዝ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ በ24 ማዕከላት 94 የተለያዩ አገልግሎቶች በተሳለጠ መልኩ እየተሰጡ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ እንግዳየሁ፣ የአገልግሎት ብክነትና ሌብነት በመቀነስ የተገልጋዮችን እርካታ 99.4 በመቶ ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።
የአገልግሎት ጥራትን በተጨማሪ ለማሻሻል ከግል ዘርፉና ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር መሥራት ወሳኝ ነው ብለዉ በዚህ መሠረትም ከልዩ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር ጋር በመተባበር ለሠራተኞች የቁጠባና የብድር አገልግሎቶችን ለማመቻቸት ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸዉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ማህበሩ በራሱ ወጪ ለመሶብ ሠራተኞች የሥራ ተነሳሽነትና የአፈጻጸም አቅምን ለማሳደግ ስልጠና ማዘጋጀቱን በማድነቅ፣ ተመሳሳይ የትብብር ሥራዎች በቀጣይም እንዲጠናከሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የልዩ የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተክሌ ሞላ በበኩላቸው፣ ማህበሩ ከተመሠረተ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ220 በላይ ሠራተኞችን በማቀፍ 11 ቅርንጫፎችን በመክፈት አባላቱንና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
ለሲዳማ መሶብ አንድ ማዕከል ሠራተኞች የተዘጋጀው ስልጠና ሠራተኞች ስለማህበሩ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ፣ የቁጠባና ብድር አገልግሎቶችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና በጋራ በመሥራት የሠራተኞችን የኑሮና የሥራ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያግዝ መሆን አስረድተዋል።
አካሉ ጥላሁን
ለሃሳብ ልዕልና
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook: -
https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944
YouTube: -
https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5
Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia
WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB
የከሸፈው የግብጽ፣ የሻዕቢያና የህወሓት ኢትዮጵያን የማዳከምና የማፍረስ ሴራ!
የክልሉ የሰላም ተምሳሌትነት ዘላቂ እንዲሆን ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው-የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
19ki Gobboomu Baandiru Barra IFDR Pirezidaantich Noowa Iibbadu Amanyootinni Ayirrinsanni
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ ጋር ውይይት አደረጉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሹመቶች ሰጥተዋል
የአውሮፓ ኅብረት አዲስ ለተመሠረተው የመደመር መንግሥት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፦
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፡-
ምክር ቤቱ የፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ
አዲስ የተመረጡት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የሥራ ርክክብ አደረጉ
አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ
የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ዛሬ ይካሄዳል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በባሕር ዳር ከተማ ቁልፍ የልማት ቦታዎችን ጎበኙ
የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ የኢሬፈና (ምስጋና ማቅረብ) ሥነ ሥርዓት
አቶ መምሩ ሞኬ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
Xaphoomu Ministerich Abiy Ahimed (Dr.) Keeniya Ei
የሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገቡ እውቅና ተሰጠው።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 27 ዳኞችን ሹመት አፀደቀ።
ምክር ቤቱ የዋና ኦዲተር ሪፖርትን አፀደቀ ።
ለጤና ባለሙያዎች አዲስ ፍቃድና ማሳደስ፣የትምህርት ማስረጃ መስጠት እና የመድሀኒትና ምግብ ቁጥጥር ስራዎችን በጥሩ አፈጻጸም መፈጸም መቻሉን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ቁጥጥር ባለሥልጣን ገለጸ።
በመስቀል አደባባይ እየተከበረ የሚገኘው የመስቀል ደመራ በዓል ድባብ
ደመራ — የመስቀሉ ብርሃን
የሀገር ሉዓላዊነት ጥበቃ በድንበርና በአየር ክልል ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂና መረጃን በስልት መጠቀምም የዘመኑ ቁልፍ የሉዓላዊነት ጥበቃ መሆኑን የሲዳማ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ገለጸ።
የመደመር አንቀጽ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ የጋራ ፕሮጀክት ይፋ የሚሆንበትን መድረክ ይታደማሉ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ጥሪ አቀረቡ
አዲሱ መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይመሰረታል - አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
ሲዳማ ብሔር ከደቡብ ኢትዮጵያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ወንድም ህዝቦች የዘመን መለወጫ በዓላትን አክብረዋል
በዝቅተኛ ኑሮ ምክንያት ለተለያዪ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች ዘላቂ መፍትሔ ለመፍጠር እየተሠራ ነዉ ፦ የፌደራል የከተሞች ምግብ ዋስትና ልማታዊ ሴፍትኔት ጸህፈት ቤት
Hawaasi Quchumi Giddo Manna Shaate Jaddo Loosse Wirri Yitino Huluullamaano Harancho Yanna Giddo Seeru Hundaanni Hossino
የሲዳማ ብሔር ተወካዮች በግፋታ
ግፋታ የአንድነትና የፍቅር በዓል በመሆኑ ለሀገራችን አንድነት መሠረት ነው -ጥላሁን ከበደ
ግፋታ የአንድነትና የፍቅር በዓል በመሆኑ ለሀገራችን አንድነት መሠረት ነው -ጥላሁን ከበደ
በህዝቦች መካከል የሚሰሩ በጎ ተግባራት አብሮነትን ያጠናክራሉ_ አስፋው ጎኔሶ
የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሀዋሳ ከተማ በድምቀት ተከበረ
ተናግሮ ማድረግ ፣ ቃል ገብቶ መፈጸም !