የክልሉ የሰላም ተምሳሌትነት ዘላቂ እንዲሆን ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው-የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

የክልሉ የሰላም ተምሳሌትነት ዘላቂ እንዲሆን ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው-የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

የክልሉ የሰላም ተምሳሌትነት ዘላቂ እንዲሆን ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው-የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ 

*********


ሀዋሳ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤስቢሲ) በክልሉ የሰላም ተምሳሌትነት ዘላቂ እንዲሆን ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል ።


ቢሮው በክልሉ ወቅታዊ የሰላም ጉዳዮች ላይ ከዞኖች፣ ከከተማ አስተዳደሮች እና ከወረዳዎች ከተወጣጡ አመራሮች ጋር መክረዋል ።


በመድረኩ የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ቶርባ እንደተናገሩት ክልሉ በሰላምና ጸጥታ ተምሳሌት እንዲሆን የክልሉ ነዋሪዎች ከመንግሥት ጋር በመቀናጀት የላቄ ድርሻ ነበረው ብለው ዘላቂ ሰላም እንዲሆን ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል ።


ሰላም ከሁሉ ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑንና የጋራ ስራ ነው ያሉት አቶ ወንድሙ በቅርቡ በተቋቋመው አድሱ መንግስት የተመደበው አድሱ አመራር ከሁሉም መዋቅር ጋር የሚሰራበት አቅጣጫ ለማስቀመጥና ለመተዋወቅ የተዘጋጀ መድረክ ነው ብለዋል።


ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ትላንት ያለፍናቸው መንገዶች ብቻ ዋስትና አይሆኑም ያሉት ኃላፊው አሰራሮችን በማዘመን፣ ተክኖሎጂዎችን በማስፋት፣ ከህብረተሰቡ ጋር ያለን ግንኙነት እና አመራሩን ይበልጥ ለማጠናከር ይሰራል ለዚህም ህብረተሰቡ እንደሁልጊዜው ከጎናችን ሊሆን ይገባልም ብለዋል።


በመድረኩ ከተሳተፉ አመራሮችም ለኤስቢሲ አስተያየታቸውን የሰጡት እንደተናገሩት ለሰላሙ ህብረተሰቡ ዘብ እንዲቆም በማቀናጀትና አሰራርን በመሻሻል ለመተግበር የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ።

በይስሐቅ ፍቅሩ



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ