የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፡-

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፡-

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፡-


የአፍሪካን ነገ ለመቀየር የሕጻናትን ጤና ማረጋገጥ ወሳኝ ነው።


ዛሬ የኢትዮጵያና ናይጄሪያ የሥርዓተ ምግብ አመራር የልምድ ልውውጥ መድረክን ከናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ካሺም ሼቲማ እና ከፍተኛ ልዑካናቸው ጋር በይፋ አስጀምረናል። 


ኢትዮጵያና ናይጄሪያ በስትራቴጂካዊ አጋርነት የተሣሠሩ ሲሆን፣ የሁለቱ ሀገራት ሰፊ የሕዝብ፣ የሰው ሀብትና የኢኮኖሚ ዐቅም በተቀናጀ ጥረት ሲመራ ለአፍሪካ ዕድገትና ብልጽግና ትልቅ ዕድል ይፈጥራል። ናይጄሪያ በሰቆጣ ቃል ኪዳን ያመጣነውን ተጨባጭ ተሞክሮ ለመቅሰም ያደረገችው ጉብኝትም የዚህ አጋርነት ተጨባጭ መገለጫ ነው።


ሥርዓተ ምግብ የጤና ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የሰው ሀብት ልማት፣ የትምህርት ውጤት፣ የምርታማነት ዐቅምና የወደፊት ብልጽግና መሠረት ነው። ስለዚህ የሥርዓተ ምግብ ጉዳይ በከፍተኛ የፖለቲካ አመራር፣ በተቀናጀ የመንግሥት ሥራና በተጠያቂነት መመራት ይገባዋል።


ባለፉት 10 ዓመታት በሰቆጣ ቃል ኪዳን የጀመረችውን ጉዞ በጠንካራ ፖለቲካዊ አመራር፣ በተቋማዊ አሠራር፣ በየደረጃው በሚደረግ ክትትልና በተቀናጀ የበጀት ምደባ በማስፋፋት ተጨባጭ ውጤት አስመዝግባለች።

 

የኢትዮጵያና ናይጄሪያ የመሪዎች የልምድ ልውውጥ ይህን ተሞክሮ ከማካፈል ባለፈ የሁለቱን ሀገራት አቅም በማቀናጀት ለጤናማ፣ ምርታማና ብልፅግናዋን ለምታረጋግጥ አፍሪካ የጋራ መፍትሔ ለመፍጠር ዕድል ይከፍታል።


የሕፃናት የዛሬ ጤና የአፍሪካ የነገ ዐቅም ነው። በዚህ እምነት የሁለቱን ሀገራት ትብብርና የመሪዎችን ቁርጠኝነት በማጠናከር፣ ለጤናማና ምርታማ ትውልድ ጠንካራ መሠረት እንጥላለን።



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ