ደመራ — የመስቀሉ ብርሃን

ደመራ — የመስቀሉ ብርሃን

ደመራ — የመስቀሉ ብርሃን


ደመራ በኢትዮጵያ ከሚከበሩ ጥንታዊና ታላላቅ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ ሲሆን፣ ከመስቀል በዓል ታሪክና ከመስቀሉ መገኘት ጋር የተያያዘ ትልቅ መንፈሳዊ ትርጉም ይዟል።


ንግሥት እሌኒ የጌታችን መስቀል የተቀበረበትን ቦታ ለማግኘት በተጠቀመችበት የእሳት ምልክት የተያያዘው ታሪክ የደመራ መነሻ እንደሆነ ይነገራል።


 በዚህም ደመራ የመስቀሉን መገኘት በደስታ የሚዘክር የእምነት ሥርዓት ሆኖ ተላልፏል።


በዋዜማው ምሽት የሚደመረው እንጨት፣ የሚበራው እሳት፣ የሚዘመረው ዝማሬና የሚደረገው ሥርዓተ ሃይማኖት የኢትዮጵያን ጥንታዊ ባህል፣ እምነትና ትውፊት በአንድ ላይ የሚያስተሳስር ውብ ትዕይንት ነው።


ደመራ የእሳት ብርሃን ብቻ አይደለም፤ የእምነት ብርሃን፣ የተስፋ ምልክትና ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የታሪክ ማስታወሻ ነው።


#SBC



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ