‎ለጤና ባለሙያዎች አዲስ ፍቃድና ማሳደስ፣የትምህርት ማስረጃ መስጠት እና የመድሀኒትና ምግብ ቁጥጥር ስራዎችን በጥሩ አፈጻጸም መፈጸም መቻሉን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ቁጥጥር ባለሥልጣን ገለጸ።

‎ለጤና ባለሙያዎች አዲስ ፍቃድና ማሳደስ፣የትምህርት ማስረጃ መስጠት እና የመድሀኒትና ምግብ ቁጥጥር ስራዎችን በጥሩ አፈጻጸም መፈጸም መቻሉን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ቁጥጥር ባለሥልጣን ገለጸ።

‎ለጤና ባለሙያዎች አዲስ ፍቃድና ማሳደስ፣የትምህርት ማስረጃ መስጠት እና የመድሀኒትና ምግብ ቁጥጥር ስራዎችን በጥሩ አፈጻጸም መፈጸም መቻሉን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ቁጥጥር ባለሥልጣን ገለጸ።


*************

ሀዋሳ- መስከረም 16/01/2019 ዓ.ም(ኤሲቢስ)

‎

‎በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና በ2019 በጀት ዓመት የሥራ እቅድ ዙሪያ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ ግብዓት ቁጥጥር ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ውይይት አካሂዷል።

‎

‎

‎የጤና ባለሙያዎች አቅምን ማሳደግ፣ የጤና ተቋማትን ግንባታና ማሻሻያ፣ የሕክምና አገልግሎትን ማዘመን፣ የሕክምና ጥራትና ደህንነትን ማረጋገጥ እንዲሁም የምግብና የምግብ ውጤቶች ጥራት ቁጥጥር ላይ በርካታ ሥራዎችን ባለፈዉ በጀት ዓመት መሥራት መቻሉን የገለጹት፣የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በጤና ዘርፉ በተከናወኑ ሥራዎች የጤና አገልግሎት ሽፋንና ጥራት ለማሻሻል የተለያዩ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

‎

‎የጤና ተቋማትን ዲጂታላይዜሽን ለማስፋፋት ከ2019 በጀት ዓመት ጀምሮ ትኩረት ተሰጥቶ እደሚሰራ ተገልጿል።


‎በጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ዘርፍ የፍቃድ አሰጣጥን በመሶብ አንድ ማዕከል በመስጠት አገልግሎትን የማፈጠን ሥራ ተሰርቷል ብለዉ የመድኃኒት ስርጭትንና አገልግሎትን ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

‎

‎በክልሉ የጤና አገልግሎት ተቋማት በተወሰነው የጥራት ደረጃና ስታንዳርድ መሠረት እንዲሠሩ ክትትልና ድጋፍ መደረጉም ጠቅሰዉ በ2021 ዓ.ም. የጤና ተቋማትን በሙሉ ወደ ተሟላ የጥራት ደረጃ ለማድረስ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል።

‎

‎

‎የሲዳማ ክልል ጤና እና ጤና ነክ አገልግሎትና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቡሪሶ ቡላሾ፣ በ2018 ዓ.ም. ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የተለያዩ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል።

‎

‎በዓመቱ ለ2 ሺህ 183 የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፍቃድ በመስጠት 100 በመቶ አፈጻጸም መመዝገቡን፣ ለ6 ሺህ 140 በላይ የጤና ባለሙያዎችን ፍቃድ እድሳት መደረጉን ገልጸዉ ለ54 የጤና ባለሙያዎች የትምህርት ማስረጃ ለመስጠት እቅድ ተይዞ ለ197 ባለሙያዎች ሥልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል።

‎

‎ 13 መካከለኛ ክሊኒኮችና 3 ልዩ ክሊኒኮች የጤና አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ፍቃድ ተሰቷል ብለዋል።

‎

‎በክልሉ ከሚገኙ ጠቅላላ 7 ሆስፒታሎች መካከል 5ቱ ጠቅላላ ሆስፒታሎች በአረንጓዴ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

‎

‎የሕክምና መሣሪያዎችንና መድኃኒቶችን ከሕገወጥ ዝውውር ለመከላከል፣ ሕጋዊና ሕገወጥ የመድኃኒት ንግድን ለመለየት እንዲሁም ጥራታቸውን ለመቆጣጠር የክትትል ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ጠቅሷል።

‎

‎ባለስልጣኑ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የዲጂታላይዜሽን ሥራ ከ2019 በጀት ዓመት ጀምሮ በትኩረት እየሠራ መሆኑም ገልጿል።

‎

‎በመድረኩ ከሀዋሳ ከተማ፣ከአራቱም ዞኖችና ከሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ የጤናዉ ዘርፍ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

‎

‎አካሉ ጥላሁን


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ