በህዝቦች መካከል የሚሰሩ በጎ ተግባራት አብሮነትን ያጠናክራሉ_ አስፋው ጎኔሶ

በህዝቦች መካከል የሚሰሩ በጎ ተግባራት አብሮነትን ያጠናክራሉ_ አስፋው ጎኔሶ

በህዝቦች መካከል የሚሰሩ በጎ ተግባራት አብሮነትን ያጠናክራሉ_ አስፋው ጎኔሶ

*************

ሀዋሳ- መስከረም 8 /1/2019 ዓ.ም(ኤሲቢስ)


 "በወንድማማችነት የተገነባ አንድነት!!" በሚል መሪ ሀሳብ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ወጣቶች በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ የተለያዩ ድጋፍ አድርጓል።


በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አስፋው ጎኔሶ ሁለቱም ክልሎች በማህበራዊና በኤኮኖሚ ጉዳዮች ጠንካራ ትስስር እንዳላቸው ገልፀው መቻቻልንና አብሮነትን ለማጠናከር በጎ ተግባራት ወሳኝ መሆናቸውን ተናግሯል ።


ወጣቶች ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልፀው አልባሌ ቦታ ከመዋል ይህንን እምቅ አቅም በመጠቀም እራሣቸውንና ሀገርን ለመለወጥ ድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል ።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ወጣቶች ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል ።


ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ፃዲቁ ባጥሶ በጎ ተግባር በህብረተሰቡ መካከል መረዳዳትንና መተሳሰብን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል ።


ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ተግባር ወጣቶች ያደረጉት ድጋፍ በሁለቱም ክልሎች መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናክራልም ብለዋል።


ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ በረከት ከዲር በበኩላቸው በመደመር ዕሳቤ በመደጋገፍ ትልቅ ለውጥ እየመጣ ባህልም እየሆነ እንደሚገኝ ተናግሯል ። በጎ ተግባር ህዝብ ለህዝብ ትስስርና አብሮነትን ለማጠናከር ዋና መሰሶ እየሆነ ይገኛልም ብለዋል።


 አቶ ደሳለኝ ደምሴ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ብዙ አቅመ ደካማ ህብረተሰብ ክፍሎችን ማገዝ መቻላቸውን ገልፀው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ ወጣቶች ይሄንን ተግባር እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል ።


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ