የሀገር ሉዓላዊነት ጥበቃ በድንበርና በአየር ክልል ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂና መረጃን በስልት መጠቀምም የዘመኑ ቁልፍ የሉዓላዊነት ጥበቃ መሆኑን የሲዳማ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ገለጸ።

የሀገር ሉዓላዊነት ጥበቃ በድንበርና በአየር ክልል ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂና መረጃን በስልት መጠቀምም የዘመኑ ቁልፍ የሉዓላዊነት ጥበቃ መሆኑን የሲዳማ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ገለጸ።

የሀገር ሉዓላዊነት ጥበቃ በድንበርና በአየር ክልል ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂና መረጃን በስልት መጠቀምም የዘመኑ ቁልፍ የሉዓላዊነት ጥበቃ መሆኑን የሲዳማ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ገለጸ።


*************

ሀዋሳ- መስከረም 14/01/2019 ዓ.ም(ኤሲቢስ)


የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ባራሳ ከSBC ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር፣ ሲዳማም እንደ ክልል በቴክኖሎጂ ዘርፍ ብቁና ንቁ ዜጎችን በማፍራት፣ እንዲሁም ለዲጂታል ምህዳሩ አስቻይና አስተማማኝ ሁኔታዎችን በመፍጠር ላይ ከፍተኛ የፖሊሲ ትኩረት ሰጥተው በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል።


ዓለም በዲጂታል መረብ ላይ በምትሽከረከርበት በዚህ ዘመን፣ የሐገራት ድንበር ጥበቃና በአጠቃላይ የደህንነት ጉዳይ፣ ከየብስ እና ከአየር አልፎ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂና መረጃዎች አጠቃቀም ተሸጋግሯል። 


ይህንን አዲስ የይዞታ ማስከበር ትግል እና የሉዓላዊነት መስመር የሚያሰምረው ደግሞ "ዲጂታል ሉዓላዊነት" የተሰኘው ሀሳብ ነው፤ ይህም ሐገራት የራሳቸውን የመረጃ ደህንነት፣ የቴክኖሎጂ መሰረተ- ልማትና የተቋሞቻቸውንና የዜጎቻቸውን የሳይበር ምህዳር በራሳቸው አቅምና ሙሉ ቁጥጥር የመጠበቅና የማስተዳደር መብትን አጉልቶ ያሳያል።


ኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነቷንና የመረጃ መሠረተ ልማቷን ከሳይበር ጥቃት ለመጠበቅ የሳይበር ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ወቅቱ የሚጠይቀው ዋነኛ አጀንዳ መሆኑን በቅጡ ተረድታለች።


የሲዳማ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ባራሳ ከSBC ጋር በነበራቸው ቆይታ የዲጂታል ሉዓላዊነት ስንል ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን የመጠበቅ አቅም መፍጠር እንደሆነ ተናግረው፣ ይህንንም ለማሳካት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።


ዲጂታል ሉዓላዊነት ማለት እንደ ሐገር የኢትዮጵያን እንዲሁም እንደ ክልል የሲዳማ ክልልን የየዘርፉን፣ ሁሉን አቀፍ፣ ስትራቴጂያዊ መረጃዎችን ለይቶ ከማወቅ እንደሚጀምር አስረድተው፣ የመረጃውን ደህንነት መጠበቅ ደግሞ ቀጣዩ ደረጃ እንደሆነ ገልጸዋል።


በዲጂታል ቴክኖሎጂ አማካኝነት ሐገሩን የሚጠብቅና ወደፊት የሚያራምድ ትውልድ መፈጠር አለበት በሚል ጽኑ እምነት የ7 ሚልዮን ኮደርስ ሥልጠና በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉን ገልፀው፣ ሥልጠናውን ያጠናቀቁ ወጣቶችም በክልሉ የተለያዩ መስኮች ላይ፣ ተሰማርተው፣ ባዳበሩት ዲጂታል ክሕሎት የበኩላቸውን አስተዋዕፆ በማበርከት ላይ እንደሚገኙ አሳውቀዋል።


አቶ ተፈራ ባራሳ፣ የቴክኖሎጂ እና የዲጂታል መረጃ አጠቃቀም የግንዛቤና የመሠረታዊ ክሕሎት እጥረት ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።


እንደ መፍትሄም ለዚህ የዲጂታል ዘመን ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን እና ባጠቃላይም ዜጎችን ለማፍራት ኤጀንሲው የሥልጠና እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብሮችን ለሕብረተሰቡ እንደሚያደርስ አስረድተዋል።


በማርያማዊት ብፅዓተ


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ