‎የከሸፈው የግብጽ፣ የሻዕቢያና የህወሓት ኢትዮጵያን የማዳከምና የማፍረስ ሴራ!

‎የከሸፈው የግብጽ፣ የሻዕቢያና የህወሓት ኢትዮጵያን የማዳከምና የማፍረስ ሴራ!

‎የከሸፈው የግብጽ፣ የሻዕቢያና የህወሓት ኢትዮጵያን የማዳከምና የማፍረስ ሴራ!

‎********

‎የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ በውጭ ጫና በውስጥ ፈተና የማይቆም የሕዝብ የጽናት፣ የአንድነትና የሉዓላዊነት ትግል ነው!

‎

‎ኢትዮጵያ የልማትና የብልጽግና ጉዞዋን ለማስቀጠል በምታደርገው ጥረት፣ የተለያዩ የውጭ ጫናዎችና የውስጥ ፈተናዎች ሲያጋጥሟት ቆይተዋል።

‎

‎የሀገሪቱን የልማት ራዕይ ለማደናቀፍ፣ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለማስተጓጎልና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም ለማዳከም የተደረጉ ጥረቶችም በተለያዩ ወቅቶች ታይተዋል። ሆኖም ኢትዮጵያ የገጠሟትን ችግሮች ተቋቁማ የልማት ጉዞዋን ለማስቀጠል የምታደርገው ጥረት ቀጥሏል።

‎

‎ቅጥረኞቹ የኢትዮጵያን የመልማትና የማደግ ራዕይ ለማደናቀፍ  የተለያዩ ጥረቶችን ብታደርግም በጀግናዉ የሃገር መከላከያ ሠራዊትና በሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ቆራጥ ተጋድሎና ጀግንነት የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ማስቆም አልቻሉም።

‎

‎ግብጽ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን ከማድረግ አልፋ ብድርና ዕርዳታ እንዳታገኝ በርካታ ተጽእኖዎችን ብትፈጥርም  ግድቡ ኃይል እንዳያመነጭ ማስቆም አልቻለችም።

‎

‎ሻዕቢያና ህገወጡ የህወሃት ቡድንን በመርዳት የከሰረችዉ ግብጽ በቅርቡ የኢትዮጵያን የባህር በር ጉዞ ለማደናቀፍ ጽምዶ የሚባል አላማ ቢስ ጥምረት ብትፈጥርም ጥምረቱ እርስ በርሱ መግባባት  አለመቻሉም አስመራንና ካይሮን እረፍት እየነሳ መሆኑንም መረጃዎች ያመላክታሉ።

‎

‎የኢትዮጵያን መዳከም እና መበታተን ከሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር፣ ሀገርን በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ እና በፕሮፓጋንዳ ለማፈራረስ ሌሊት ከቀን ሠርቷል። 

‎

‎ግብጽ እነዚህንና መሠል እኩይ  ስልቶችን ተጠቅማ ኢትዮጵያን ለማዳከምና በቀጣናዉ ያላትን ተቀባይነት ይበልጥ ለማጠናከር በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ብታፈስም እኩይ ፍላጎቷን ማሳካት አልቻለም።

‎

‎ይልቁንም የኢትዮጵያ መንግስት ይዞ የተነሳዉ ታላቋን ኢትዮጵያ የመገንባት እና ብልጽግናን የማረጋገጥ ራዕይ ለፈርዖኖቹ ትልቅ ስጋት ሆኗል።

‎

‎ግብጽ የሃገሬ ብሄራዊ ጥቅም የሚረጋገጠዉ የኢትዮጵን ሉዓላዊነትና ህልዉናን በመገዳደር እንዲሁም የሃገሪቱን ሠላምና ልማት በማደናቀፍ ነዉ የሚል እኩይ አላማ አላት።

‎

‎ይህንን እኩይ አላማዋን የሚያስፈጽሙላት ደግሞ እንደ ሻዕቢያ፣ ህገወጡ የህወሃት ቡድንና ጽምዶ ያሉ ቅጥረኞች ናቸዉ።

‎

‎የጥፋት ሃይሎቹ ከግብጽ በሚሰጣቸዉ  ተልዕኮ፣ የበጀትና የቁሳቀስ ድጋፍ ላለፉት ስልሳና ሰባ አመታት የገዛ ሃገራቸዉን ለማፈራሰስ ሲታትሩ ኖረዋል።

‎

‎በተለይ ሻዕቢያ ፈርዖኖቹን በታማኝነት የሚያገለግል የጥፋት መልዕክተኛ  ሲሆን ለግብጽ ያለዉን ታማኝነት ለማረጋገጥ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል፣ ኢትዮጵያም የባህር በር እንድታጣ አድርጓል። 

‎

‎ሻዕቢያ ኢትዮጵያን የባህር በር አሳጥቶ ግብጾችን ከማስደሰትና የኢትዮጵያዊያንን የኑሮ ጫና ከማባባሱ በስተቀር የባህር በሩን ተጠቅሞ የገዛ ዜጎቹን ህይወት  መለወጥም ሆነ ኤርትራን ማበልጸግ አልቻለም።

‎

‎በሻዕቢያ ተጸንሶ  በኤርትራ ምድር የተወለደዉ ህገወጡ የህወሃት ቡድንም ቢሆን የኢትዮጵያን የዕድገት ጉዞ ለማደናቀፍ ለሻዕቢያና ለፈርዖኖቹ  በታማኝነት ከመላላክ ዉጭ በትግራይ ክልል ዘላቂ ሠላምና ልማትን ማረጋጠጥ አልቻለም። 

‎

‎ቡድኑ ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማስተጓጎል የተቻለዉን ሁሉ ቢያደርግም  የፈርዖኖቹን የጥፋት ተልዕኮ ማሳካት አልቻለም።

‎

‎ኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ ያጣችዉን የባህር በር ሕጋዊና ሠላማዊ በሆነ መንገድ ለማስመለስ የጀመረችዉን እንቅስቃሴ ተከትሎ  በካይሮና አስመራ ትልቅ ድንጋጤ ተፈጥሯል። 

‎

‎በሃገሩ ሉዓላዊነትና ህልዉና የማይደራደረዉ ጀግናዉ የሃገር መከላከያ ሠራዊት ከለዉጡ በኋላ የገነባዉ ትልቅ ወታደራዊ አቅምም የምስራቅ አፍሪካን ሠላምና ደህንነት ማረጋገጥ የሚችል አስተማማኝ ሃይል መሆኑም በቀጣናዉ ለሚንቀሳቀሱ የጸረ ሠላም ሃይሎች ትልቅ ስጋት ሆኗል።

‎

‎የሠራዊቱ ጀግንነት እና ስልታዊ ጥቃት የከሃዲውን ስብስብ እቅድ ያፈራረሰ ሲሆን፤ ቡድኑ በጦር ግንባር መቋቋም አቅቶት ወደ መፈርጠጥ ገብቷል። 

‎

‎ይህ መፈርጠጥ ተራ ሽንፈት ብቻ ሳይሆን፤ የተቋሙን የሞራል እና የታሪክ ውድቀት ጭምር አጉልቶ ያሳየ ነው።

‎

‎በገዛ እናት ሀገር ላይ ክህደት ፈጽሞ በድል መውጣት እንደማይቻል፣ ይልቁንም ታሪካዊ ውርደትን ተከናንቦ በሕዝብ ዘንድ መወገዝን እንደሚያተርፍ ይህ ቡድን ሕያው ምስክር ነው። 

‎

‎አካሉ ጥላሁን


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.co


‎


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ