‎በዝቅተኛ ኑሮ ምክንያት ለተለያዪ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች ዘላቂ መፍትሔ ለመፍጠር እየተሠራ ነዉ ፦ የፌደራል የከተሞች ምግብ ዋስትና ልማታዊ ሴፍትኔት ጸህፈት ቤት

*************

ሀዋሳ- መስከረም 11/01/2019 ዓ.ም(ኤሲቢስ)

‎

‎የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና ሥራ ፕሮጀክት የ2019 እቅድ ማናበብና የ3ኛ ዙር የተጨማሪ ፋይናንስ ዕቅድ ዝግጅት ግምገማ መድረከ በሀዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

‎

‎በጉባኤው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የፈደራል የከተሞች ምግብ ዋስትና ልማታዊ ሴፍትኔት ጸህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ብርሀኑ ተሾመ ፕሮጀክቱ በዚህ አመት ከ420 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል ፡፡

‎

‎ፕሮጀክቱ የድሀ ድሀ የተባሉ ዜጎችን ማገዝና ስራ እንዲለማመዱ ማድረግ እንድሁም ለወጣቶች ሙያ አሰልጥኖ ስራ ማስጀመሪና የተለያዩ ዘርፈ ብዙ የአከባቢ ማህበረሰብ ተኮር ስራዎች ላይም ትኩረት አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል ።

‎

‎በመድረኩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ብሩክ ሠለሞን በኘሮጀክቱ ድጋፍ በክልሉ ውስጥ በከተሞች ልማታዊ ሴፍትኔት በሚደገፉ ከተሞች ውስጥ ብዙ ሥራዎች መሠራቱን ጠቁመዋል ፡፡

ሰይፉ ዳዊት

ለሃሳብ ልዕልና 

ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 

Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB

‎

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ