በጤናው ዘርፍ ያስመዘገብናቸው አበይት ስኬቶች ለድንገተኛ አደጋዎች ያለንን ዝግጁነት ያረጋገጡ ናቸው፦ ዶክተር መቅደስ ዳባ ******************** የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ኮሚቴ 76ኛ መደበኛ ስብሰባን ለማስተናገድ የመዲናችን አዲስ አበባ በር ክፍት ሲሆን፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ባደረጉት ንግግር የአህጉራችንን የጤና ወደፊት የሚቀርጽ ራዕይ ይፋ አድርገዋል። ባለፉት ዓመታት በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡት ስኬቶች የቃል ኪዳናችን ማረጋገጫዎች መሆናቸውን ያብራሩት ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ ኢትዮጵያ በጤና ትራንስፎርሜሽን በኩል ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች የመልካም አስተዳደርና የቁርጠኝነት ማሳያዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። ዶክተር መቅደስ ዳባ እንዳመለከቱት፣ የወረርሽኝ ስጋቶችን አስቀድሞ የመለየት አቅም ከ65 በመቶ ወደ 95 በመቶ ማደጉ፣ የፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድኖች ሽፋን ወደ 93 በመቶ ከፍ ማለቱ፣ እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ተደራሽነት 86.3 በመቶ መድረሱ ኢትዮጵያ ለድንገተኛ የጤና አደጋዎች ያላትን ዝግጁነት ያረጋገጡ አበይት እርምጃዎች ናቸው። ከ69 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ሚኒስትሯ አብራርተዋል። ሆኖም ግን የዘመናዊው ዓለም ተግዳሮቶች አሁንም ከፊታችን ተደቅነው እንደሚገኙ ዶክተር መቅደስ ዳባ አሳስበዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች፣ ያልተመጣጠነ የሀብት ክፍፍል፣ የዲጂታል ክፍተቶችና የአቅርቦት ሰንሰለት ጥገኝነት ለአህጉራችን አዲስ የቤት ሥራ መስጠታቸውን የጠቀሱት ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ በዲጂታል ዘመን እኩልነት ማለት በከተማና በገጠር የሚኖሩ ማህበረሰቦች እኩል የጤና እንክብካቤ አገልግሎት ማግኘት አለባቸው ብለዋል። አፍሪካ ከውጭ እርዳታ ጥገኝነት ተላቃ የራሷን የሀገር ውስጥ መድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች የማምረት አቅም ማሳደግ እንዳለባት የገለጹት ሚኒስትሯ ኢትዮጵያም የሀገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾችን የገበያ ድርሻ በማሳደግ ረገድ ያሳየችው አወንታዊ ጭማሪ ለቀጣናው አባል ሀገራት አርአያ የሚሆን ተሞክሮ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በቂ እውቀት፣ አቅምና የፖሊሲ ፍላጎት እንዳላት የገለጹት ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ አሁን የሚያስፈልገው ይህንን አቅም ወደ ዘላቂ የጤና ደህንነትና ሉዓላዊነት የሚቀይር አህጉራዊ አንድነት እንደሆነ ተናግረዋል። እናቶች ከወሊድ አደጋ የሚተርፉበት፣ ሕፃናት አድገው ለወደፊት ተስፋ የሚበቁበት፣ እና የጤና ባለሙያዎቻችን በክብር ህዝባቸውን የሚያገለግሉበትን አህጉራዊ ሥርዓት ለመገንባት ኢትዮጵያ ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን የጀመረችውን የመሪነት ሚና አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑን ዶክተር መቅደስ አረጋጠዋል።(ኢቢሲ)ቦታዎችን ጎበኙ

በጤናው ዘርፍ ያስመዘገብናቸው አበይት ስኬቶች ለድንገተኛ አደጋዎች ያለንን ዝግጁነት ያረጋገጡ ናቸው፦ ዶክተር መቅደስ ዳባ

********************

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ኮሚቴ 76ኛ መደበኛ ስብሰባን ለማስተናገድ የመዲናችን አዲስ አበባ በር ክፍት ሲሆን፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ባደረጉት ንግግር የአህጉራችንን የጤና ወደፊት የሚቀርጽ ራዕይ ይፋ አድርገዋል። 

ባለፉት ዓመታት በጤናው ዘርፍ የተመዘገቡት ስኬቶች የቃል ኪዳናችን ማረጋገጫዎች መሆናቸውን ያብራሩት ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ ኢትዮጵያ በጤና ትራንስፎርሜሽን በኩል ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች የመልካም አስተዳደርና የቁርጠኝነት ማሳያዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። 

ዶክተር መቅደስ ዳባ እንዳመለከቱት፣ የወረርሽኝ ስጋቶችን አስቀድሞ የመለየት አቅም ከ65 በመቶ ወደ 95 በመቶ ማደጉ፣ የፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድኖች ሽፋን ወደ 93 በመቶ ከፍ ማለቱ፣ እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ ተደራሽነት 86.3 በመቶ መድረሱ ኢትዮጵያ ለድንገተኛ የጤና አደጋዎች ያላትን ዝግጁነት ያረጋገጡ አበይት እርምጃዎች ናቸው። 

ከ69 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ሚኒስትሯ አብራርተዋል። ሆኖም ግን የዘመናዊው ዓለም ተግዳሮቶች አሁንም ከፊታችን ተደቅነው እንደሚገኙ ዶክተር መቅደስ ዳባ አሳስበዋል። 

የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች፣ ያልተመጣጠነ የሀብት ክፍፍል፣ የዲጂታል ክፍተቶችና የአቅርቦት ሰንሰለት ጥገኝነት ለአህጉራችን አዲስ የቤት ሥራ መስጠታቸውን የጠቀሱት ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ በዲጂታል ዘመን እኩልነት ማለት በከተማና በገጠር የሚኖሩ ማህበረሰቦች እኩል የጤና እንክብካቤ አገልግሎት ማግኘት አለባቸው ብለዋል። 

አፍሪካ ከውጭ እርዳታ ጥገኝነት ተላቃ የራሷን የሀገር ውስጥ መድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች የማምረት አቅም ማሳደግ እንዳለባት የገለጹት ሚኒስትሯ ኢትዮጵያም የሀገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾችን የገበያ ድርሻ በማሳደግ ረገድ ያሳየችው አወንታዊ ጭማሪ ለቀጣናው አባል ሀገራት አርአያ የሚሆን ተሞክሮ መሆኑን ጠቁመዋል።

አፍሪካ በቂ እውቀት፣ አቅምና የፖሊሲ ፍላጎት እንዳላት የገለጹት ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ አሁን የሚያስፈልገው ይህንን አቅም ወደ ዘላቂ የጤና ደህንነትና ሉዓላዊነት የሚቀይር አህጉራዊ አንድነት እንደሆነ ተናግረዋል። 

እናቶች ከወሊድ አደጋ የሚተርፉበት፣ ሕፃናት አድገው ለወደፊት ተስፋ የሚበቁበት፣ እና የጤና ባለሙያዎቻችን በክብር ህዝባቸውን የሚያገለግሉበትን አህጉራዊ ሥርዓት ለመገንባት ኢትዮጵያ ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን የጀመረችውን የመሪነት ሚና አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑን ዶክተር መቅደስ አረጋጠዋል።(ኢቢሲ)

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ