የሲዳማ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በሀዋሳ ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን እና የሀይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ።

የሲዳማ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በሀዋሳ ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን እና የሀይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ።
የሲዳማ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በሀዋሳ ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን እና የሀይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን ጎበኙ።
********
ሀዋሳ፣ ነሐሴ 20/2018 ዓ/ም (ኤስቢሲ)
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በሀዋሳ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት እና የሀይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን ሥራዎችን ጉብኝት አድርገዋል ።
በሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራዎች በተለያዩ ምዕራፎች ተከፋፍለው እየተከናወኑ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ሦስተኛ ምዕራፎች ተጠናቀዋል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ አራተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።
አመራሮቹ በጉብኝታቸው በአራተኛው የኮሪደር ልማት ስራ አካል የሆነውን 1.4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ከጥቁር ውሃ እስከ ሀይሌ ሪዞርት የሚዘልቀውን የአስፋልት መንገድና የኮሪደር ልማት ሥራ ፤ 12 ኪሜ ርዝመት ያለውን የሀይቅ ዳርቻ ልማት ስራን ተመልክተዋል።
እነዚህ የልማት ስራዎች ለከተማዋ ነዋሪዎች ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለቸው የገለጹት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የክልሉ መንግሥት ለልማቱ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም መላው የህብረተሰብ አካል፣ የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች ከተማዋን የሚወዱ አካላት በፋይናንስ ድጋፍ በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፣ በመሆኑም የተጀመሩት የልማት ሥራዎች በአጭር ጊዜ እንደሚጠናቀቁ ጠቁመዋል።
ሀዋሳን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን የገለጹት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የከተማን ገጽታ ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ያደረጉ የኮሪደር ልማትና የአስፖልት መንገድ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አስታውሰው።
የሀይቅ ዳርቻ ልማት ስራ በህዝብ ተሳትፎ እየተከናወነ ነው ያሉት ከንቲባው የሀይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ስራ በአጠቃላይ 3.2 ቢሊዮን ብር የሚጨርስ ሲሆን፣ እስካሁን ከህብረተሰቡ 1.5 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።
አቶ ጥራቱ አክለውም የመንግሥትና የህብረተሰቡ ተሳትፎ የተጠናከረ በመሆኑ፣ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንደሚጠናቀቁ አረጋግጠዋል ።
በጉብኝቱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ በራሳ፣ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በዚህ መርሃ ግብርም በሲዳማ ክልል በሌሎች ዞኖች የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን አመራሮቹ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በክብረበዓል መላኩ
ለሃሳብ ልዕልና
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ