የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በጤና ፕሮግራም ዘርፍ የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2019 ዓ.ም እቅድ ላይ መምከር ጀመረ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በጤና ፕሮግራም ዘርፍ የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2019 ዓ.ም እቅድ ላይ መምከር ጀመረ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በጤና ፕሮግራም ዘርፍ የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2019 ዓ.ም እቅድ ላይ መምከር ጀመረ።

****************

ሀዋሳ፣ ነሐሴ 22/2018 ዓ/ም (ኤስቢሲ) 


የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በጤና ፕሮግራም ዘርፍ የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት አመት ክንዉንና በ2019 ዓ.ም እቅድ ላይ የሚመክርበትን መርሀ-ግብር ማካሄድ ጀምሯል።


የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይነህ በቀለ በመርሀ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት በበጀት አመቱ ጥራቱን የጠበቀና ለሁሉም ፍታሃዊ ተደራሽ የሆነ የጤና ማበልፅግ እና በሽታን የመከላከልና የፈውስ ህክምና በመስጠት እና የጤና አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ በኩል በበጀት ዓመቱ መልካም ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል::


በተለይም የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው በሚገኙ የጤና ባለሙያዎች፣ በአመራር አካላት ቁርጠኝነት እንዲሁም በጤና ልማት አጋሮች ያላሰለሰ ጥረትና በማህበረሰብ ተሳትፎ የተገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል።


በ2018 በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እና የታዩ ድክመቶችን በአጭር ጊዜ በማረም የህብረተሰባችንን የጤና ተጠቃሚነት በተግባር ማረጋገጥ ይኖርብናል ያሉት አቶ በላይነህ ከክልል ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ያሉ አመራርና ባለሙያዎችን ባካተተ መልኩ የመስክ ምልከታ የሚያደርግ ቡድን መሰማራቱ ስራዎችን በጥልቀት ለመገምገም ያስችላል ብለዋል።


በተለያዩ መዋቅሮችና ቀበሌ በማህበረሰብ ውስጥ የተሰማራው ቡድን ስራዎችን በጥልቀት በማየት አስተማሪ የሆኑ ተሞክሮዎች በማየት ወደ አካባቢያቸው ለማስፋት እንደሚሰሩ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል ።


ኤርምያስ ሳንባቶ


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ