የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን ለመደገፍ የክልሉ መንግሥት ከጎኑ ይቆማል:- ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን ለመደገፍ የክልሉ መንግሥት ከጎኑ ይቆማል:- ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን ለመደገፍ የክልሉ መንግሥት ከጎኑ ይቆማል:- ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ
**********
ሀዋሳ፣ ነሐሴ 24/2018 (ኤስ ቢ ሲ)
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን ለመደገፍ በሚያስፈልገው ሁሉ የክልሉ መንግሥት ከክለቡ ጎን እንደሚቆም የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን የገለጹት ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ የእግር ኳስ መድረክ ላይ ነሀሴ 30/2018 ዓ/ም ለሚሳተፈው ለሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የጉዞ ሽኝትና የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።ክለቡ ባለፈው የውድድር ዓመት በሀገር ደረጃ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን አስታውሰው ፣ በአፍሪካ መድረክም ኢትዮጵያንና ሲዳማን በክብር እንዲወክል አደራ ብለዋል።
ክለቡ በአፍሪካ ውድድር ላይ የሚያስመዘግበው ውጤት የክለቡን ብቻ ሳይሆን የክልሉንና የሀገሪቱን የእግር ኳስ ስም ለማስጠራት ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።
ለክለቡ የሚደረገው ድጋፍ በባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ በሚከፈተው የሂሳብ ቁጥር በኩል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል ።
በመርሃ ግብሩ የሲዳማ ክልል መንግሥት የሴክተር መሥሪያ ቤቶች፣ የክልሉ ዞኖች፣ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ባለሀብቶች ባደረጉት የገንዘብ ድጋፍ 80 ሚሊዮን 400 ሺህ ብር ማሰባሰብ ተችሏል።
በታመነ አረጋ
ለሃሳብ ልዕልና
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ