የቀድሞ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ከ20 አመታት በኋላ ያገናኘው የፍቅር መሰባሰብ

የቀድሞ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን  ከ20 አመታት በኋላ ያገናኘው የፍቅር  መሰባሰብ
የቀድሞ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ከ20 አመታት በኋላ ያገናኘው የፍቅር መሰባሰብ
ሀዋሳ፣ ነሐሴ 24/2018 ዓ/ም (ኤስቢሲ) የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የተመሰረተው በ1994 አመተ ምህረት ነበር። በወቅቱ ደቡብ ዩኒቨርስቲ በሚል ስያሜም ይታወቅ ነበር። ባለፉት 24 አመታት 120ሺህ ተማሪዎችን በተለያዩ ሙያዎች አስተምሮ ለወግ ማዕረግ አብቅቷል።
የቀድሞ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አብዛኞቹ በአሁን ወቅት በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ በመሰማራት ሀገርና ወገንን እያገለገሉ ነው።
በከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊነት እስከ ሚንስቴር የደረሱ ናቸው። ዲፕሎማቶች ፣የዩኒቨርስቲ መምህራን እና ተመራማሪዎች ታዋቂ ደራሲያንና ጋዜጠኞች ሆነዋል።
በተለይም 1994 አመተ ምህረት የመጨረሻው በቀድሞ የትምህርት ስርዐት የመጨረሻው የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ተፈታኞች በዩኒቨርስቲው የተለየ ቦታ አላቸው ።
ከ1994 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የገቡ የቀድሞ ተማሪዎች ከመላው አለም በመሰባሰብ የጋራ ማህበር አቋቋመዋል።
የማህበሩ የመጀመሪያው የጋራ መድረክ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በድምቀት ተካሄዷል ።
የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕረዚዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የቀድሞው የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ፍሬዎች ወደ ቤታቸው በመመለሳቸው ዩኒቨርስቲው ኩራት ይሰማዋል ብለዋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የምስረታውን 50ኛ አመቱን ለማክበር እየተዘጋጀ መሆኑን ያነሱት ፕረዚዳንቱ የቀድሞው ተማሪዎች የክብረ በዓሉ አካል እንዲሆኑ ጋብዘዋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲውም ሆነ የሃዋሳ ከተማ አምባሳደሮች መሆናቸውንም አንስተዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳና የቀድሞ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ምሩቅ የሆኑት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከመጀመሪያዎቹ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች መካከል አንዱ መሆናቸውን በማስታወስ የቀድሞ ተማሪዎች በዚህ መልክ በመሰባሰባቸው ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል ።
የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ባለፉት አመታት በርካታ ለሀገር ጠቃሚ ስራ የሰሩ ዜጎችን ማፍራት መቻሉን በማንሳት እንዲህ በህብረት መሰባሰቡ ለሀዋሳ ብሎም ለኢትዮጵያ ትልቅ አቅም ይኖረዋል ብለዋል።
ሀዋሳ ለቀድሞ ልጆቿ ሁሌም በሯ ክፍት ነው ያሉት ከንቲባው በሀዋሳ ለመስራትና ለመለውጥ ፣በንግድና ኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ብሎም ለመኖሪያነት ለመረጡ ሁሉ የከተማ አስተዳደሩ ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ መስራች ፕረዚዳንት ፕሮፌሰር ዝናቡ ገብረማርያም በቀድሞ ተማሪዎች ክብር ስላገኙ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው በማንሳት የሀዋሳ ዩኒቨርስቲም ሆነ የሀዋሳ ከተማ ዘርፈ ብዙ ለውጥ በአስደናቂ ሁኔታ እያመጡ መሆናቸውን በማንሳት ይሄም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል
።
የሀዋሳ ሀይቅ የሀዋሳ ከተማ ህልውና መሆኑን በመጥቀስ ሁሉም ልማቶች የሀይቁን ደህንነት በግምት ያስገባ እንዲሆን ጠይቀው በሀዋሳ ከተማ ለግማሽ ክፍለ ዘመን መኖራቸውን በማንሳት ለከተማዋ የተለየ ፍቅር አለኝ ብለዋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ ምሩቃን ማህበር ሰብሳቢ ዶክተር እመቤት በቀለ በበኩላቸው ይህ ማህበር የተቋቋመው በመጀሪዎቹ የዩኒቨርስቲው ምሩቃን መሆኑን በማንሳት በተለያዩ ማህብረሰቡን፣ ዩኒቨርስቲውንና ከተማዋን በሚጠቅሙ ተግባራት ውስጥ ለመሳተፍ ዕቅድ መኖሩን አመልከተዋል ። የወቅቱን ተማሪዎች የትምህርት ቤት ትዝታዎችን የያዘ መፅሐፍም በመድረኩ ተመርቋል።
SBC ያነጋገርናቸው የቀድሞ ምሩቃን እንደተናገሩት በሀዋሳ ከተማ ፍፁማዊ ለውጥና በዩኒቨርስቲው ዕድገት መደነቃቸውን ተናግረዋል ።
በመላው አለም ያሉ ምሩቃን የካበት የህይወት ልምድና ኢንቨስት የማድረግ አቅም ላይ የደረሱ በመሆኑ በከተማዋ በተለያዩ የስራ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለቸው ተናግረዋል ።
ከአመታት በኋላ ወደ ሀዋሳ ሲመለሱ ለተደረገላቸው ልባዊ አቀባበል አመስግነው ወደ ቤታቸው በመመለሳቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
የቀድሞ ምሩቃን ችግኞችን በመትከል ፣የእግር ጉዞ በማድረግ እና የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በጀማል የሱፍ
ለሃሳብ ልዕልና
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ