በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ ወሰን ተሻጋሪ የወጣት በጎ ፍቃደኞች በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ሀዋሳ ከተማ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መረሃ ግብር አካሄዱ።

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ ወሰን ተሻጋሪ የወጣት በጎ ፍቃደኞች በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ሀዋሳ ከተማ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መረሃ ግብር አካሄዱ።

''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ ወሰን ተሻጋሪ የወጣት በጎ ፍቃደኞች በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ሀዋሳ ከተማ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መረሃ ግብር አካሄዱ።

*********

ሀዋሳ: ነሀሴ 26/2018 ዓ.ም (ኤስ ቢ ሲ)  

‎

‎በሀገር አቀፍ ደረጃ ወሰን ተሻጋሪ የሆኑ ወጣቶች ከያሉበት የማህበረሰብ ክፍል ተወጣጥተው፣ ወደ ተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በመንቀሳቀስ የበጎ አላማ ተግባር በማከናወን ላይ ይገኛሉ።

‎

‎በዘንድሮ አመትም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለአምስተኛ ዙር የበጎ ፍቃደኞች ቡድን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሰላሳ ሁለት በላይ ብሔር ብሔረሰቦች የተወጣጡ በጎ ፍቃደኞች ሀዋሳ ከተማ ሲደርሱ በክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ ወጣቶቹም የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን እከናውነዋል።

‎

‎በመረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ እመቤት ኢሳያስ እንዳሉት፣ የበጎነት ስራ በገንዘብ የሚለካ አለመሆኑን አንስተው ይህ ተግባር ከምንም በላይ ፍቅርን በማስተማር አንድነት እና ህብረትን እንደሚያጠናክር ገልፀዋል።

‎

‎በክልላችን በጎ ተግባር ማከናወናቸው የመተሳሰብን፣የመረዳዳትን፣ የአብሮነትን እና የአንድነት እሴቶች በተግባር ለማጠናከር ገንቢ ሚና እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ወጣቶቹ በቆይታቸውም የከተማ ጽዳት፣ የደም ልገሳ፣የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ፣ የማዕድ ማጋራትን ጨምሮ በጎ ተግባራትን በማከናወን በማህበረሰቦች መካከል ወዳጅነትን በማጠናከር እና የልምድ ልውውጥን አድርገዋል ። 

‎

‎ወሰን ተሻጋሪ ወጣቶቹ በዛሬው እለት የበጎ ፍቃድ ስራዎችን ያከናወኑ ሲሆን በቀጣይነትም ወደሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በመጓዝ ልምዳቸውን እና የበጎነት ተመሳሌትነታቸውን የሚያካፍሉ ይሆናል ።

‎

‎በኪሩቤል ፈለቀ


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB1o



‎


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ