የበለጸገች ሀገር ለመገንባት፣ ድህነትን ለመቀነስና የመንግስት አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ ዘርፎች ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ። ‎

የበለጸገች ሀገር ለመገንባት፣ ድህነትን ለመቀነስና የመንግስት አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ ዘርፎች ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።  ‎

‎ የበለጸገች ሀገር ለመገንባት፣ ድህነትን ለመቀነስና የመንግስት አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ ዘርፎች ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

‎

**********

ሀዋሳ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም(ኤስቢሲ)


‎የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ የISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ትግበራ ሰርቲፊኬት ባለቤት በመሆኑ በተዘጋጀ የእውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል ።

‎

‎የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ

‎ሀገራችንን በአጭር ጊዜ የምታድግና የበለጸገች ሀገር ለማድረግ በተቀመጡ የልማት አቅጣጫዎች መሠረት በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑና ውጤቶችም እየተመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል።

‎

‎በተለይም ዜጎች የመንግስት አገልግሎቶችን ሳይንገላቱ በቀላሉ፣ በፍጥነትና በጥራት እንዲያገኙ የተቋማት ሪፎርምና የአገልግሎት ማሻሻያ ሥራዎች ተጠናክረው እየተሰሩ መሆኑንም አስረድተዋል።

‎

‎ርዕሰ መስተዳደሩ የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች በትብብር በመሥራት ለሥራ ምቹ የሆነ የተቋም አካባቢ ለመፍጠር ያከናወኑትን ሥራ አድንቀዋል።

‎

‎ቢሮው በጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ተመዝኖ የISO 9001:2015 ሰርቲፊኬት ባለቤት መሆኑ ለሌሎች የክልሉ ተቋማት ጠቃሚ ተሞክሮ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

‎

‎ ሌሎች ቢሮዎችም ይህንን ተሞክሮ በመውሰድ የተቋማት ሪፎርምና የአገልግሎት ጥራት ሥራዎቻቸውን ማጠናከር እንደሚገባ አመልክተዋል።

‎

‎የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ

‎ሀገረጽዮን አበበ ላለፉት ሁለት አመታት የሪፎርም ሥራዎችን በመስራት ዉጤት መስመዝገብ ተችሏል ብለዋል

‎

‎ቢሮዉ ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ሰርተፊኬት ባለቤት መሆኑ ገልጸዋል።


‎‎ የተቋማት ግንባታ፣ የሪፎርም ሥራዎችና ጥራት ያለው የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ ተሰርቷል ብለዋል።


‎በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዲሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዴታ ወ/ሮ ነቢያ መሐመድ በበኩላቸው፣ በተቋም ግንባታ፣ በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በሠራተኞች ሥራ ትስስር ዘርፎች በርካታ የሪፎርም ሥራዎች በውጤትና በተጠያቂነት መንፈስ እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

‎

‎ተቋም ግንባታ ለሀገር ልማትና ለዘላቂ ውጤት ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ተግባር መሆኑን ጠቅሰው፣ የሲዳማ ክልል ባለፉት አምስት ዓመታት በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ያከናወነው ሥራ ውጤታማ በመሆኑ የዋንጫ ተሸላሚ መሆኑን አውስተዋል።

‎

‎ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ፣ ጥራት ለሀገር ዕድገትና ለተቋማት ውጤታማነት መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

‎

‎ጥራትን የሥራ ባህል ማድረግ እንደሚገባና በሀገሪቱ የጥራት ባህልን ለማስፋፋት በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

‎

‎ሁሉም ተቋማት ለጥራት ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ገልጸዉ፣ የምርትና የአገልግሎት ጥራት ደረጃዎችን በተገቢው ለመተግበር ሠራተኞችን ማሰልጠን፣ የአመራር ቁርጠኝነትን ማጠናከርና የደንበኞችን ፍላጎትና ግብረመልስ በቀጣይነት መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።


አካሉ ጥላሁን


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB


‎

‎

‎


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ