ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ10 የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 1500 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ10 የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 1500 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ10 የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ 1500 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

*********  

ሀዋሳ፣ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም(ኤስ ቢ ሲ)


በምረቃው መርሀ ግብር ላይ የሲዳማ ክልል ስራና ከህሎት ቢሮ ሀላፊ ሀገረፅዮን አበበን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እንደሀገር ሰፊ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን የተናገሩት የክልሉ የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ ሀገረ ፂዮን አበበ በኮሌጁም ገበያውን መሰረት ያደረገ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።


ሀገርንና አለምን የሚቀይር ልዩ ተሰጥኦ የመፍጠር አቅምን ማጎልበት የሚቻልበት ጊዜ ላይ ነን ሲሉም የሙያውን ተፈላጊነት አረጋግጠዋል።


ከ 90 በመቶ በላይ የሚሆኑ ተመራቂዎች ከስራ ጋር መገናኘታቸውን በማንሳት ሙያተኞቹ በቀጣይ ባገኙት እውቀት ታግዘው ለሀገር ልማት እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።


የኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ በራሳ በበኩላቸው ዘመኑን የዋጀ ብቃት ያለው ዜጋ ለማፍራት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።


 ሰልጣኞች ከኢንዱስትሪው ጋር የሚገናኙበትና ወደ ስራ የሚገቡበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም አንስተዋል።


ከአጠቃላይ ሰልጣኞች አንደኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ የሆኑት ተመራቂ ጣሀ ሰይድና ዲቦራ አህመድ የተፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ሀገራቸውን በትጋት ለማገልገል መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።


ሳሮን ኢሳያስ 


ለሃሳብ ልዕልና 


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB



አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ