‎በበዓላት ወቅት ሸማቾች ከገበያ የሚገዙዋቸውን የምግብ ነክ ምርቶች በጥንቃቄ መምረጥ እንደሚገባ የሲዳማ ክልል ጤና እና ጤና ነክ የእቃዎች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሀላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ ገለጹ።

‎በበዓላት ወቅት ሸማቾች ከገበያ የሚገዙዋቸውን የምግብ ነክ ምርቶች በጥንቃቄ መምረጥ እንደሚገባ የሲዳማ ክልል ጤና እና ጤና ነክ የእቃዎች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሀላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ ገለጹ።
‎በበዓላት ወቅት ሸማቾች ከገበያ የሚገዙዋቸውን የምግብ ነክ ምርቶች በጥንቃቄ መምረጥ እንደሚገባ የሲዳማ ክልል ጤና እና ጤና ነክ የእቃዎች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሀላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ ገለጹ።
‎************
ሀዋሳ:- ጳጉሜ 02/13/2018 ዓ/ም(ኤስ ቢ ሲ)
‎ባለስልጣኑ የኢትዮጵያ አዲስ አመት ሲከበር ህብረተሰቡ ማድረግ ስለሚገባዉ የጤና ጥንቃቄ ለSBC መግለጫ ሰጥተዋል።
‎
‎የሲዳማ ክልል ጤና እና ጤና ነክ የእቃዎች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሀላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ በበዓል ወቅት በብዛት ከሚገዙ የምግብ ምርቶች መካከል ቅቤ፣ በርበሬ፣ ጤፍ፣ ማርና ዘይት ይገኛሉ ብለዉ፣ እነዚህ ምርቶች በቀጥታ ከሰው ጤና ጋር የተያያዙ በመሆናቸው ሸማቾች ከማይታመኑ ምንጮች ምርቶችን ከመግዛት መቆጠብ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
‎በተለይ በበርበሬ እና በሌሎች የዱቄት ምርቶች ውስጥ የጤና ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ባዕድ ነገሮች ሊቀላቀሉ ስለሚችሉ፣ ሸማቾች ምርቶችን ከመግዛታቸው በፊት ጥራታቸውን በመመርመር እንዲገዙ ሀላፊው አሳስበዋል።
‎
‎
‎ለበዓሉ የስጋ ፍጆታ የሚጨምር በመሆኑ፣ ሸማቾች ለእርድ የሚውሉ እንስሳት የጤና ምርመራ የተደረገላቸውና ጤናማ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገልጿል።
‎
‎የእንስሳት ጤና ሁኔታ ሳይረጋገጥ እርድ ማካሄድ በሰው ጤና ላይ አደጋ ሊያመጣ ስለሚችል፣ በእርድ ወቅት የእንስሳት ጤና ምርመራን ተገቢውን ቦታ መስጠት እንደሚገባም ጠቁመዋል ።
‎
‎ከዚህ በተጨማሪ ስጋ በሚዘጋጅበትና በሚበላበት ወቅት የንጽህና ሁኔታን መጠበቅ፣ የምግብ አያያዝን በአግባቡ ማካሄድና የምግብ ብክለትን መከላከል የሁሉም ሸማችና የቤተሰብ አባል ኃላፊነት መሆኑ ተገልጿል።
‎በበዓሉ የሚፈጠረው የደረቅና የፍሳሽ ቆሻሻ በአግባቡ ካልተወገደ ለአካባቢ ብክለትና ለተለያዩ የጤና ችግሮች ሊዳርግ እንደሚችል ገልጸዉ፤
‎በመሆኑም ቤተሰቦች የሚያመነጩትን ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ በተገቢው መንገድ ማስወገድ፣ የእርድ ተረፈ ምርቶችን በየቦታው ከመጣል መቆጠብና የአካባቢን ንጽህና መጠበቅ እንደሚገባ ሀላፊው አሳስበዋል።
‎በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምግቦች በብዛት የሚዘጋጁ በመሆናቸው፣ ምግብን በመጠኑ መመገብ፣ ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች ከመጠን በላይ ከመመገብ መቆጠብና ለጤናማ አመጋገብ ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ አስረድተዋል።
‎
‎የጤና ነክ ምርቶችንና የምግብ ምርቶችን በተመለከተ መረጃ ያላቸው ዜጎች በነጻ ስልክ መስመር 7732 በመደወል መረጃ መስጠትና ጥያቄዎችን ማቅረብ እንደሚችሉ ሀላፊው ገልጸዋል።
‎
‎አካሉ ጥላሁን
ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎

አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ