የወጣቶችን የሲቪክ ተሳትፎና ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የወጣቶችን የሲቪክ ተሳትፎና ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የወጣቶችን የሲቪክ ተሳትፎና ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።


**************

ሀዋሳ:- ጳጉሜ 03/13/2018 ዓ/ም(ኤስ ቢ ሲ)


 የወጣቶችና ባህል ልማት ፋውንዴሽን (YCDF) ወጣቶች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳዮች ያላቸውን ተሳትፎ በማጠናከር ማህበራዊ ትስስርን፣ ሰላምንና የማህበረሰብ ልማትን ለማጎልበት ያለመ የሦስት ዓመት ፕሮጀክት አስጀምሯል።


 በሲቪል ሶሳይቲ ኢኖቬሽን ፈንድ ሁለተኛ ዙር (CSIF II) ስር የሚተገበር ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በአምስት ክልሎች በሚገኙ 16 ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ ወረዳዎች ይተገበራል።


ፕሮጀክቱ ከ18–35 ዓመት ዕድሜ የሚገኙ 5,000 ወጣቶችን በቀጥታ የሚያሳትፍ ሲሆን፣ ወጣቶች በሲቪክ ተሳትፎ፣ በአመራር፣ በጥብቅና፣ በማህበራዊ ተጠያቂነት፣ በሰላም ግንባታና በውይይት ያላቸውን አቅም እንዲያሳድጉ ያግዛል።

 

የYCDF የሲዳማ ክልል ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ግሩም ሙሉጌታ በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ በሰጡት አስተያየት፣ YCDF ፕሮጀክቱን ከኦ-ዬስ (O-YES)፣ ጌትስ ፎር ኦፖርቹኒቲ (Gates for Opportunity) እና እኛ ለእኛ (Ega Lega) የወጣቶች ጤናና ልማት ድርጅት ጋር በትብብር እየተገበረ መሆኑን ገልፀው ፕሮግራሙ በሲዳማ ክልል በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር እና በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ወጣቶች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ ጉዳዮችና በስነ-ልቦና የበለጠ የጠነከሩ እንዲሆኑ ፕሮጀክቱ ሰፊ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።


የሲዳማ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊና የገንዘብና አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሸንካራ ሾዴ በበኩላቸው፣ ወጣቶች በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስተጋብሮች ተጠቃሚና ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ከመንግስት ጥረት በተጨማሪ የአጋር ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።


አቶ ሸንካራ እንደገለጹት፣ የመንግስትን ጥረት በማጠናከር የሚሰሩ የሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶችና ሌሎች የልማት አጋሮች ወጣቶች የራሳቸውን አቅም እንዲጠቀሙና በሀገር ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል ጠቃሚ አስተዋፅኦ አላቸው።


የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከዚህ በፊት በወጣቶች ላይ የነበሩ ልክ ያልሆኑ አመለካከቶች እየተለወጡ መምጣታቸውን ተናገረው ለዚህም "YCDFP" ፕሮግራም የወጣቱን ንቃተ ህሊና በማሳደግ ሰፊውን ስራ እንደሰራ ተነግረዋል ።


በኤርምያስ ሳንባቶ


ቀጣዮቹን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የኤስቢሲ ቤተሰብ ይሁኑ! 


Facebook: -

https://www.facebook.com/profile.php?id=61563363361689 https://www.facebook.com/profile.php?id=100064075051944

YouTube: -

https://youtu.be/fUjnn1dQLg8?si=1bzb_8Nx8mnC-Vk5

Telegram: - https://t.me/sbcnewmedia

WhatsApp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaZ2D6NH5JLsF9xJaB




አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ