ከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ዘርፎች የታቀዱ እቅዶች ለመፈጸም በተደረገ ሰፊ ጥረት በስድስት ወር ውስጥ አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል :-ከንቲባ ጥራቱ በየነ

ከተማ  አስተዳደሩ በሁሉም ዘርፎች የታቀዱ  እቅዶች  ለመፈጸም በተደረገ ሰፊ ጥረት በስድስት  ወር ውስጥ አመርቂ  ውጤት አስመዝግቧል :-ከንቲባ ጥራቱ በየነ

በተደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ ውጤቶች በተለይ በኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ አበረታች ለውጦች ተመዝግቧል ። የስራ ባህላችን ተቀይሮ 7/24 መሰራት መጀመሩ ፤በከተማዋ የሚከበሩ ሀይማኖታዊ በዓላት በሰላም መጠናቀቃቸውን እንደስኬት የሚታይ መሆኑን ከንቲባው ገልፀዋል ።
የሀብት ብክነትንና ከብልሹ አሰራር የፀዳ ወጪን በማስቀረት ገቢን በተገቢው በመጠቀም ከተማችንን ማልማት እንደሚጠበቅብንም አፅንኦት ሰጥተዋል።
በሌላ በኩል አሁንም ያልተሻገርናቸው ብልሹ አሰራር ፣ የውሸት ሪፓርት ከመታገል አንፃር ያሉብንን ችግሮች ለመቅረፍ ከወትሮ በተለየ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል እንደሚገባም ከንቲባው ተናግረዋል።
በተጨማሪም የከተማችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለቅመን አሁን በጀመርነው መሠረት በመለየት ፈጣን ምላሽ በመስጠት የህብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ ይኖርብናል ነው ያሉት።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ