ሀብት ለማፍራትና የዜጎችን እርካታ ለማረጋገጥ በስራ እድል ፈጠራ ላይ በቅንጅት መምራት ያስፈልጋል

ሀብት ለማፍራትና የዜጎችን እርካታ ለማረጋገጥ በስራ እድል ፈጠራ ላይ በቅንጅት መምራት ያስፈልጋል

ሀብት ለማፍራትና የዜጎችን እርካታ ለማረጋገጥ የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በቅንጅት መምራት ያስፈልጋል ሲሉ የሲዳማ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ተናግረዋል።
የሲዳማ ክልል የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት በ2018 ዓ.ም የ7 ወር አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የሲዳማ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደገለጹት የስራ እድል ፈጠራ ጉዳይ በአንድ ተቋም ብቻ የሚፈጸም ሳይሆን ሁሉም ሴክተሮች በስራቸው ላይ የወጣቶችን የስራ እድል ታሳቢ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
ትኩስ ኃይል የሆኑ የተማሩትን ወጣቶች ሀብት ማፍራት እንዲችሉ ክህሎት መሪ ስልጠና ወስደው ወደ ኢንዱስትሪው እንዲገቡ ጠንካራ አመራር ያስፈልጋል ያሉት ፕሬዚደንቱ በተለይም ብድር ማቅረብና ማስመለስ፣ የገጠማቸው ተግዳሮትም ለመፍታት የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤቱ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል
የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረፅዮን አበበ በበኩላቸው ክህሎት መሪ የስራ እድል መተግበር ከተጀመረ ወዲህ የተሻለ አፈፃፀም ተመዝግበዋል ብለው፣ በዚህም ስልጠናን ማዕከል በማድረግ ለወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸው ሀብት ማፍራት መቻላቸውን ተናግረዋል።
ይህም በበጄት ዓመቱ ባለፉት ሳባት ወራት የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም በሚቀጥለው አንድ ውር የታቀዱትን በፍጥነት ለማከናወን የሚያስችል ግምገማ ነውም ብለዋል።
በመድረኩ ከክልል፣ ከዞኖች፣ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና ከወረዳዎችና ከተለያዩ ተቋማት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ስሆን ውይይቱ እየቀጠለ ነው።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ