ከጥቂት ወራት በፊት በሲዳማ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስን ከባለድርሻ አካላት ጋር በተሰራው ስራ ለመቆጣጠር ተችሏል -ፕረዚዳንት አቶ ደስታ ለዳሞ

ከጥቂት ወራት በፊት በሲዳማ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስን ከባለድርሻ አካላት ጋር በተሰራው ስራ ለመቆጣጠር ተችሏል -ፕረዚዳንት አቶ ደስታ ለዳሞ

የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ለመቆጠር በተሰራው ስራ የድርሻውን ለተወጡ አካላትና ተቋማት የምስጋናና የዕውቅና ሴርትፊከት ተሰጥቶአል ።
የሲዳማ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ደስታ ለዳሞ እንደተናገሩት ከጥቂት ወራት በፊት በሀዋሳ ከተማ በአንድ ግለሰብ ላይ ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስን በጠንካራ አስተዳደር ምሪት ከሕብረተሰቡ ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ከጤና ተቋማት ፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት በተሰራው ስራ ቫይረሱ ወደሌላ ሕብረተሰብ ክፍል ሳይዛሜት መቆጣጠር መቻሉን ገልጸዋል ።
ፕረዚዳንቱ አክለውም ቫይረሱን ለመቆጣጠር የድርሻቸውን ለተወጣጡ አካላት በክልሉና በራሳቸው ስም አመስግነዋል።
የኢፌዴሪ ጤና ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ የማርበርግ ቫይረስ በኢትዮጵያ በጂንካ ተከስቶ የነበረው በሀዋሳም ስከሰት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሕዝብን የሚያደነጋግር የሐሰት ወሬ ብሰራጭም በፈጣሪ እገዛና በተባበረ ክንድ ቫይረሱን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል ።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሰላማዊት መንገሻ በበኩላቸው የማርበርግ ቫይረስ ከኮቪድ ቀጥሎ አደገኛ ገዳይ በሽታ መሆኑን ገልጸው በክልሉ ከአንድ ሰው ሞት በቀር ተጨማር ሞት ሳይከሰት የፈጣሪ እገዛ ታክሎበት በቁጥጥር ስር መዋሉን አስገንዝበዋል ።
በተለይ ከሞት ጋር በመጋፈጥ ቯይረሱ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ለተወጡ ለዘርፉ ባለሙያዎች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ