ከMarch 8 የቀደመች የሲዳማዋ ንግስት ፉራ

ከMarch 8 የቀደመች የሲዳማዋ ንግስት ፉራ

ዛሬ የካቲት 29 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እየተከበረ ነው። ይህ ቀን ታሪካዊ መነሻው የሴት ሠራተኞች በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1908 "የስራ ሰዓት ይሻሻልልን፣ የተሻለ ክፍያ ይገባናል፣ ሴቶችም በምርጫ መሳተፍ አለባቸው" በማለት እንቅስቃሴ የጀመሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዕውቅና የተሰጠው ዓመታዊ በዓል ለመሆን በቅቷል።
ዓለም ማጀትን ለሴት አደባባይን ለወንድ በሸለመችበት ቀደም ባለው ጊዜ የሲዳማ ህዝብ ግን የሴት ልጅን የጥበብ መሪነትን በንግስተ ፉራ በኩል ለዓለም አሳይቶዋል።
ንግስት ፉራ ከሲዳማ ምድር የተገኘች የሴቶችን ጭቆናና በደል በመቃወም ለበርካታ ሴቶች የብልሃተኝነትን ሀሁ ከ ሴትነት አድባር ስር ያስተማረች ድንቅ የሲዳማ ንግስት ናት።
ብልሃተኝነቷ ከልጅነት ጀምሮ የነበረና በለጋ እድሜዋ ሳይቀር ብልሃትን ለሽማግሌዎች ያስተማረች እንደነበረች ይህ ታሪክ ያሳል።
አንድ በሲዳማ የነበረ ንጉስ መልክተኞችን እናቱን እንዲጠይቋት ይልካል ታድያ እንቆቅልሽ የሆነ ነገር ይነግራቸዋል። "የእናቴን ዜና ስትነግሩኝ በሂወት አለችም ሞታለችም ሳትሉ ንገሩኝ "አላቸው በዚህም አዋቂ የሚባሉ ሽማግሌዎች ሲጨነቁ ያየችው ብልሃተኛዋ ትንሿ ፉራ ጉዳዩን ጠየቀች እያመነቱ ሲነግሯት ልጅነት ያልጋረደውን ብልሃትዋን ተጠቅማ ላስጨነቃቸው ጥያቄ መልሱን ነገረቻቸው "ፀጉራችሁን አንዱን ጎን ተላጭታችሁ ሌላውን ጎን አጎፍራችሁ ሂዱ "እናቴ ሞታለች ወይ ?” ካለ “ብትሞት አጎፍረን እንመጣለን “በሉ በሂወት አለች ወይ ካለ ደግሞ “በሂወት ብትኖር እንላጭ ነበር ወይበሉ"በማለት ብልሃትን በልጅነትዋ ለሽማግሌዎች አስተማረች።
ንግስተ ፉራ ሴቶች በትዳራቸው ብልሃተኛ እንዲሆኑም የሴትን ብልሃትን እንዲህ ስትል መክራች ይባላል ''ጎመን ስትቀቅሉ፣ ቅቤ ስታነጥሩ፣ ወተት ስትንጡ፣ እንሰት ስትፍቁ… ወዘተ. ከወንዶች ዓይን ደብቁ፡፡ ምክንያቱም አብዛኞቹ የምግብ ዓይነቶች ብዙ የነበረው መጠናቸው ከበሰለ በኋላ ስለሚያንስ ወንዶቹ ''ከምንጊዜው አለቀ? በማለት እንዳይወቅሱዋችሁ ያስችላል'' ብላቸው ነበር ይባላል፡፡
ስለዚህ አብዛኛዎቹ የሲዳማ ሴቶች እስከዛሬ ድረስ ይህንን ልማድ ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡
ንግስት ፉራ የሴቶችን ጭቆና ና የበታችነት ለማስወገድ በብዙ የጣረች አለም March 8 መርጦ ለሴቶች መሟገት ሳይጀምር ቀድማ የሴትን ልጅ መብት ያስጠበቀች ሴቶች በመሪነት መሳተፍ እንደሚችሉ ከዘመን በፊት ሰልጥና ያስተማረች ድንቅ የሲዳማ ንግስት ናት።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ