የትግራይ ሕዝብ ሰላምና ዕረፍት ይሻል፤ ወጣቱ ሥልጣን ሊረከብ ይገባል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

የትግራይ ሕዝብ ሰላምና ዕረፍት ይሻል፤ ወጣቱ ሥልጣን ሊረከብ ይገባል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በትግራይ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ የትግራይ ሕዝብ የሚገባው ሰላም፣ ዕረፍትና ልማት እንጂ ዳግም ጦርነት እንዳልሆነ አሳሰቡ።
የትግራይ ሕዝብ ሰላምና ልማት የሚገባው፣ የሚወድና ለእነዚህ እሴቶችም የታገለ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአንጻሩ ጦርነትና ውድመት እንደማይገባው ጽኑ እምነታቸውን ገልጸዋል።
ይህ ሰላምና ልማት በአሮጌ አስተሳሰብ ሊረጋገጥ እንደማይችል የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሥልጣን የሕዝብ በመሆኑ አመራሩ በተማሩ ወጣቶች እጅ ሊሆን እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በእርጅና ዘመናቸው ጦርነት የሚቀሰቅሱ መሪዎችን ሕዝቡ 'ሥልጣን ይበቃችኋል፤ ለልጆቻችሁ አስረክቡ' ሊላቸውና ለሰላም ያለውን ጽኑ ፍላጎት በግልጽ ሊያሳውቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በሌሎች ክልሎች የታየው ሰላምና ልማት ለትግራይም እንደሚገባው በመጥቀስ፤ "ከሰላም ፈላጊና ከተማሩ ወጣቶች ጋር በመተባበር ለትግራይ ሰላምና ልማት እንሥራ" የሚል ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ ስብራት ለመጠገን አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት በውይይትና በሰላም ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ