ፊቼ ጫምባላላ ለአንድነትና ለእድገት በሚል መሪ ቃል የህዝብ ውይይት መድረክ በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ ።

ፊቼ ጫምባላላ ለአንድነትና ለእድገት በሚል መሪ ቃል  የህዝብ ውይይት መድረክ በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ ።

የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ የአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት "ፊቼ ጫምባላላ ለአንድነትና ለእድገት" በሚል መሪ ቃል መድረኩ ተካሂዷል።
‎በዓሉ እሴቱን ጠብቆ ከወትሮው በተለየ ድምቀት እንዲከበር በከተማ ደረጃ በቂ ዝግጅት መደረጉን የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገልፀዋል።
‎ፊቼ ጫምባላላ ከባህላዊና ህዝባዊ እሴቱ በተጨማሪ የከተማችንን የቱሪዝም ዘርፍ በማሳደግ ሀብት የምንፈጥርበትና የገቢ አቅማችንን የምናጎለብትበት ሊሆን እንደሚገባም ከንቲባው ጠቁመዋል።
‎የዘንድሮው የፊቼ ጫምባላላ በዓል በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር እንግዶች የሚታደሙበት ሆኖ በድምቀት እንደሚከበርም ነው አቶ ጥራቱ የተናገሩት።
‎በዚህም በበዓሉ ነዋሪው የሚደምቅበት፣ የንግዱ ማህበረሰብ የላቀ አገልግሎት የሚያቀርብበት ብሎም እንግዶች ምቾታቸው ተጠብቆ የሚታደሙበት ሆኖ እንዲከበርም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ በተገቢው ሊወጣ እንደሚገባም ከንቲባው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
‎እንደ ሀዋሳ ከተማ ህዝብ ግንኙነት መረጃ ፤ መድረኩ በበዓሉ እሴቶችና በአከባበሩ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ የተፈጠረበት መሆኑን የገለፁት በውይይት መድረኩ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች በዓሉን በአብሮነትና በአንድነት ለማክበርና እንግዶችን ዳዎኤ ቡሹ ብለው ለመቀበልና የላቀ አገልግሎት ለመስጠት በላቀ ደረጃ መዘጋጀታቸውን ጨምረው ገልፀዋል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ