"ከምርጫ ድል ማግስት ጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ሀሳብ በሀዋሳ ከተማ የህዝብ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

"ከምርጫ ድል ማግስት ጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ሀሳብ በሀዋሳ ከተማ የህዝብ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

"ከምርጫ ድል ማግስት ጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ሀሳብ በሀዋሳ ከተማ የህዝብ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
‎በመድረኩ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደተናገሩት
‎ሀገራችን ድሞክራሲያዊ ምርጫ እንዳታካሂድ ከውስጥና ውጭ ኃይሎች የተለያዩ ጫናዎች ቢደርሳትም በድል በመወጣት ለኢትዮጵያ ፣ ለአፍሪካ ብሎም ለአንዳንድ የዓለም ሀገራት አርአያ የሚሆን
‎ፍጹም ሠላማዊ፣ድሞክራሲያዊና፣ተዓማኒነት ያለውን 7ተኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ ማካሄዷን ተናግረዋል።
ይህም አንዱ የስልጣኔ ምልክት መሆኑንም አንስተዋል።
‎ከምርጫ ማግሥት እንደመንግስት በምርጫ ወቅት በክልሉ ሰላም እንዲሰፍንና ዴሞክራሲ እንዲጎለብት የአንበሳውን ድርሻ የተወጣውን ህዝብ ማመስገን እና በቀጣይ ለሚሰሩ የልማት ሥራዎች የህዝብን ፍላጎት ማድመጥ የመድረኩ ዋና ዓላማዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።
‎የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው
‎ሀገራችን ላካሄደችው 7ተኛ ጠቅላላ ምርጫ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመስግነዋል። የሀዋሳ ከተማ ህዝብ ለከተማው ሁለንተናዊ እድገት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
‎ህዝብ ከተባበረ ልማትን ማስቀጠልና ብልጽግናን ማረጋገጥ ቀላል ነው ያሉት ከንቲባው ህዝቡ
‎ለምርጫው መሳካት ያሳየውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።
‎ከምርጫ ማግስት የጀመርናቸውን ልማቶች አጠናክረን እንቀጥላለንም ብለዋል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ