ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ለማዘጋጀት ከዓለም አትሌቲክስ እድል አገኘች

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ለማዘጋጀት ከዓለም አትሌቲክስ እድል አገኘች

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከ አለም አትሌቲክስ ጋር የጀመረውን የስፖርት ዲፕሎማሲ ወደ ከፍታ በማድረስ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለምአቀፍ ውድድር ለማዘጋጀት በማስቻል አዲስ ምዕራፍ አስመዝግቧል ።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለምአቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ኤፕሪል 18/2026 One day meeting በአዲስአበባ ለማዘጋጀት ዛሬ እድል በማግኘት ፣በዓለም አትሌቲክስ ካላንደር ውስጥ መካተት ችሏል ።
የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ "ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውደድሮችን ለማዘጋጀት በቂ አቅም እንዳላትና፣የተለያዩ ውድድሮችን ወደ ኢትዮጵያ እናስመጣለን ማለታቸው " የሚታወስ ነው።
ውድድሩን የዓለም አትሌቲክስ ከፍተኛ ባለሙያዎች የሚመሩት በመሆኑ ለአገራችን የአትሌቲክስ ሙያተኞች ልምድ ለማግኘት የሚያስችልና ፣ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ አትሌቶች የሚሳተፉበት ከመሆኑ ባሻገር በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች ከፍተኛ ሽልማት የሚያገኙበት ይሆናል።
በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ አለምአቀፍ ውድድር ለማዘጋጀት ያገኘነውን እድል የዓለም አትሌቲክስን በማመስገን ውድድሩን ወደ አገራችን እንዲመጣ የላቀ ሚና የተወጣችሁ በተለይም የኢፌድሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና ከፌዴሬሽኑ ጎን ለቆማችሁ ባለድርሻ አካላትን ምስጋናችን የምናቀርብ ሲሆን፣ የጀመርነውን ዓለምአቀፍ ግንኙነት እና የስፖርት ዲፕሎማሲ አጠናክረን እንቀጥላለንም ብሏል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ