የሲዳማ ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫንባላላ በዓልን መጋቢት 5 እና 6 እሴቱን ጠብቀቆ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቅቋል

የሲዳማ ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫንባላላ በዓልን መጋቢት 5 እና 6  እሴቱን ጠብቀቆ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቅቋል

‎የሲዳማ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ፤ ፍቼ-ጫምባላላ ክብረበዓል አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
‎በሲዳማ ቀደምት ሽማግሌዎች (አያንቶዎች) የስነ ከዋከብት እና ጨረቃ ምልከታ በማድረግ በዓሉ የሚከበርበትን ቀን ከመጋቢት 05_06/2018 ዓ.ም መሆን ቆርጠው ካሳወቁ በኋላ በሚከበረው በዚህ በሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓል አሮጌው ዓመት በአዲሱ የሚተካበት መሆኑን አስታውሰው በዓሉን ባህላዊ እሴቶችን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ብለዋል።
‎ፊቼ ጫምባላላ ከሲዳማ እሴትነት አልፎ በዩኔስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ባሕላዊ ቅርስ ዝርዝር መዝገብ ላይ መስፈሩን ተከትሎ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የሚታደሙት ልዩ በዓል መሆኑን ጠቁመዋል።
የሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን ‎ቢሮ መረጃ ፣ በፊቼ ጫምባላላ በዓል ቅድመ ዝግጅት የሲዳማ ሽማግሌዎች አዲሱን ዓመት የሠላም፣ የበረከት፣ የፍቅር፣ የደስታና የጥጋብ እንዲሆን ፈጣሪን በኡሱራ ጾም ጸሎት ይማፀናሉ፣ጥላቻና ቁርሾ ከቤተሰብ እስከ ማህበረሰብ የሚወገድበት፤ ሽማግሌዎች ሀገር እንዲፀና የሚማፀኑበት መሆኑን ገልፀዋል ።
‎በዓሉ ለሲዳማ ብሔር ከዘመን መለወጫነት ባሻገር ትልቅ ትርጉም ያለው የማንነቱ መገለጫ፤ የነፃነትና የፍቅር ማዕድ ሁሉም በጋራ የሚቋደስበት፤ የመንፃትና የመታደስ፤ አዲስ ተስፋ የሚሰነቅበት፣በዳኤ ቡሹ እርስ በርስ ያላቸውን ፍቅር፣አክብሮትና ደስታ የሚገልጹበት፤በውስጡ ያሉ በርካታ እሴቶች በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች የሚገለጹበት፣ እርቅ የሚፈፀምበትና ሀዘን የሚያበቃበት አልፎ ተርፎም በዓሉ ስከበርም አብሮነትን፣አንድነትን ፣ፍቅርን፣ መረዳዳትን፣ መደማመጥን እንዲሁም መተባበርን የሚያጎሉ ድርጊቶችም የሚፈጸሙበት ነው ብለዋል።
‎አቶ ጃጎ አገኘሁ በመጨረሻም የዘንድሮው በፍቼ ጫምባላላ በዓል መጋቢት 05_06/2018 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን ከወንድም ህዝቦች፣ ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች ጋር በህብረት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ገልጸው በዓሉ ለመላው ሲዳማ ህዝብ፣ለኢትዮጵያና ለዓለም ህዝቦች የሰላም፣የደስታ፣የጤና እና የብልጽግና እንዲሆን ከወዲሁ ተመኝተው በዓሉን በጋራ ማክበር፣መንከባከብ፣ማድመቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ