ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተከለሰ ዕቅድ ገመገሙ

ምድብ : ክልላዊ | ንዑስ ምድቦች : ክልላዊ ዜናዎች የተለጠፈ ጊዜ 2025-12-03 07:50:26


ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተከለሰ ዕቅድ ገመገሙ

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተከለሰ ዕቅድ ገመገሙ
*************
ሀዋሳ፣ ህዳር 13፣ 2018 (ኤስቢሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በኩል የቀረበውን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተከለሰ ዕቅድ ከክልሉ አስተባባሪ ጋር ገምግመዋል።
ግምገማው ውጤታማ አፈጻጸም እንዲኖር
ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለማቀናጀት የተካሄ ነው። የቀረበው የተከለሰ ዕቅድ እስካሁን እየተሠሩ ያሉ ጠንካራ ሥራዎችን አጠናክሮ የሚያስቀጥልና ለውጤት የሚያበቃ፣ጉድለቶችን ለይቶ የሚያርምና የሚሞላ አዳዲስ ጉዳዮችንም የጨመረ ነው።
የክልሉ አስተባባሪ ተጨማሪ ግብዓት በስጠት በፍጥነት ፈጠራ ታክሎበት ርብርብ እንዲደረግ የሥራ ባህል እንዲሻሻል በአጠቃላይ የክልሉ ክትትልና ድጋፍ እንደማይለያቸው በማረጋገጥ ወደ ሥራ እዲገቡ ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ማጠቃለያ ወቅት ገልፀዋል።

ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ
አስተያየት መስጫ