በክልሉ ያለውን የኢኮኖሚ አቅም አሟጦ ገቢ ለመሰብሰብ የገቢ አሰባሰብ ታሪፍ ለማሻሻል እየሰራሁ ነው-የሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን

ምድብ : ኢኮኖሚያዊ | ንዑስ ምድቦች : ቢዝነስ/ኢኮኖሚ የተለጠፈ ጊዜ 2025-12-03 07:54:21

በክልሉ ያለውን የኢኮኖሚ አቅም አሟጦ ገቢ ለመሰብሰብ የገቢ አሰባሰብ ታሪፍ ለማሻሻል እየሰራሁ ነው-የሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን

በክልሉ ያለውን የኢኮኖሚ አቅም አሟጦ ገቢ ለመሰብሰብ የገቢ አሰባሰብ ታሪፍ ለማሻሻል እየሰራሁ ነው-የሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን
**************
ሀዋሳ፣ ህዳር 15፣ 2018 (ኤስቢሲ) በክልሉ ያለውን የኢኮኖሚ አቅሞችን አሟጦ ገቢ ለመሰብሰብ የገቢ አሰባሰብ ታሪፍ ለማሻሻል እየሰራ እንደሆነ የሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን አስታውቋል።
ባለስልጣኑ ከሰሜናዊ ሲዳማ ዞንና ከሀዋሳ ከተማ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን አቶ ደምሴ እሳቱ እንደተናገሩት ክልሉ ካለው ሀብት ልክ የመንግስት ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለሟሟላት እንዲሆን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ክልሉ ላይ ሁሉንም የገቢ ምንጭ ለመጠቀም እንዲያመችና አሁን በምርቶችና በዕቃዎች ላይ የመጣውን የዋጋ ልዩነት ታሳቢ ያደረገ የታክስ ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉና በየደረጃው ግንዛቤ በመፍጠር ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።
በመድረኩ የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፃዲቁ ባጥሶ በበኩላቸው ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ አሁን የተጠናውን የታክስ ማሻሻያን ጨምሮ ሌሎች ገቢዎችን በቅንጅትና በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የተሳተፉ የዞንና የሀዋሳ ከተማ አመራር አካላትም የተደረገውን የታክስ ታሪፍ ማሻሻያው ተግባራዊ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ
አስተያየት መስጫ