ዛሬ ሲዳማ ቡናና ሀዋሳ ከተማ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ

ምድብ : የስፖርት | ንዑስ ምድቦች : የስፖርት ዜናዎች የተለጠፈ ጊዜ 2025-12-03 07:56:59


ዛሬ ሲዳማ ቡናና ሀዋሳ ከተማ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ

ዛሬ ሲዳማ ቡናና ሀዋሳ ከተማ ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ
**************
ሀዋሳ፣ ህዳር 17፣ (ኤስቢሲ) የፕሪምየርሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ይጫወታል፤ ሀዋሳ ከተማ ደግሞ ከፋሲል ከነማ ይፋለማል።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ሰበተኛ ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር 7:00 ይገናኛሉ ። ሁለቱም ቡድኖች ወቅታዊ አቋማቸው መልካም መሆኑ ጨዋታውን ተጠባቂ አድርጎታል ።
ሲዳማ ቡና ይሄን ጨዋታ በድል በማጠናቀቅ መሪነቱን ለማጠናከር ብርቱ ፍላጐት አለው ። መቻል በበኩሉ ከመሪዎቹ ጎራ ላለመራቅ ጠንካራ ተጋድሎ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ።
በዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ክስተት የሆነው ሲዳማ ቡና በ13 ነጥብ ውድድሩን እየመራ ነው።
ከሲዳማ ቡና በመከተል በአንድ የጎል ክፍያ ብቻ ተበልጦ በ13 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ የፕሪሚየርሊጉ ድምቀት መሆን የቻለው ሀዋሳ ከነማ በበኩሉ ከፋሲል ከነማ ጋር 10:00 ይገናኛሉ።
ያሬድ ብሩክን የመሳሰሉ ወጣቶችን ከአንጋፋዎቹ ጋር ያጣመረው ሀዋሳ ከተማ በውድድር አመቱ ምርጥ ጊዜን እያሳፈ ነው።
የሀዋሳ ከተማ ተጋጣሚ የሆነው ፋሲል ከነማ አረተኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ ጥሩ ወቅታዊ ቅርፅ ላይ እንዳለ እያሳየ ነው።
ሲዳማ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ የዛሬው ግጥሚያ በአሸናፊነት ካጠናቀቁ መሪነታቸውን አጠናክረው ማስቀጠል ይችላሉ ።


ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ
አስተያየት መስጫ