የኢትዮጵያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የህዝቦች እኩልነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሰጥበታል:: የሲዳማ ክልል ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ

ምድብ : ማህበራዊ | ንዑስ ምድቦች : ማህበራዊ የተለጠፈ ጊዜ 2025-12-03 07:59:59

የኢትዮጵያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የህዝቦች እኩልነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሰጥበታል:: የሲዳማ ክልል ም/ቤት ዋና  አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ  ፋንታዬ ከበደ

የኢትዮጵያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የህዝቦች እኩልነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሰጥበታል:: የሲዳማ ክልል ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ
**********************
ሀዋሳ፣ ህዳር 17 ፣ 2018 (ኤሲቢሲ)
ኢትዮጵያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የህዝቦች እኩልነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሰጥበታል አሉ የሲዳማ ክልል ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ።
የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ዘንድሮ ለ20ኛ ጊዜ "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት’’ በሚል መሪ ሃሳብ በሆሳዕና ከተማ ይከበራል፡፡
20ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ጠቁመው የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን ሚና ባለው መልኩ ለማጠናከርና ኅብረብሔራዊ አንድነቱን ሊያጎላ በሚችል መልኩ ማክበር እንደሚገባ ተናግረዋል።
አፌ-ጉባኤዋ ወ/ሮ ፋንታዬ አክለውም የበዓሉ አላማ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መካከል በብዝኀነት ላይ የተመሠረተ አንድነት እንዲዳብር ማድረግ እንደሆነ ገልጸው ዓላማውን ለማሳካትም አገራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ ሥራዎች ሊሰሩ ይገባልም ብለዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ ኅዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከበረውን በዓል በማስመልከት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት መድረክም በክልል ደረጃ በም/ቤቱ አዘጋጅነት ተካሂዷል።

ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ
አስተያየት መስጫ