ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ከኢትዮጵያ -ቻይና ወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤቲ ዡ ጋር በጋራ በሚሰራባቸው ጉዳዮች የማዕቀፍ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

ምድብ : ክልላዊ | ንዑስ ምድቦች : ክልላዊ ዜናዎች የተለጠፈ ጊዜ 2025-12-03 08:07:47


ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ከኢትዮጵያ -ቻይና ወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤቲ ዡ ጋር በጋራ በሚሰራባቸው ጉዳዮች የማዕቀፍ ስምምነት  ሰነድ ተፈራረሙ


ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ከኢትዮጵያ -ቻይና ወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤቲ ዡ ጋር በጋራ በሚሰራባቸው ጉዳዮች የማዕቀፍ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ
********************
የኢትዮጵያ -ቻይና ወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴ ሊቀመንበር ቤቲ ዡ የተመራ ልዑክ በዛሬው ዕለት ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ጋር በክልሉ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር የረዥም ጊዜ የወንድማማችነት እና የትብብር ታሪክ ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አስታውሰው፤ የሲዳማ ክልልም በርካታ የመልማት ፍላጎት ያለው ክልል መሆኑን ገልፀዋል። የተፈጥሮ ቡናን በማምረት በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የሲዳማ ክልል ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ያለው ክልል መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።
በክልሉ ያለው ዘላቂ ሰላም እና እምቅ አቅም በርካታ የውጪ ሀገራት ኢንቨስተሮችን እየሳበ የሚገኝ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ የገለፁ ሲሆን፤ እንግዳ ተቀባይ የሆነውን የክልሉን ህዝብ፣ የክልሉን ሰላም፣ የተፈጥሮ ፀጋዎችን፣ አምራች የሆነውን የሰው ሀይል፣ የተደራጁ ተቋማትን እና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም የቻይና ባለሀብቶች በክልሉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን ያስተላለፉ ሲሆን፤ የክልሉ መንግሥት ለአልሚ ባለሀብቶች አስፈላጊ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል።
በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ ለተገኘው የቻይና ኢንቨስተሮች ልዑክ በክልሉ ያሉ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የተመለከተ ዝርዝር ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
የቻይናው ልዑካን ቡድንም በተደረገላቸው አቀባበል እና ገለፃ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የዕድገት እና የኢንቨስትመንት ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
የዛሬው መድረክም የዚሁ አካል መሆኑን ገልፀው የቻይና ባለሀብቶች በክልሉ ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በተለያዪ ዘርፎች የኢንቨስትመንት በመሠማራት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስገኘት እንደሚሰሩ ነው ያስረዱት።
በተለይም በግብርናው፤ በማዕድን፤ በሶላር ኢነርጂና እና ሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ለመሰማራት ያላቸውን ፍላጎትና ዝርዝር ዕቅድ ለክልሉ መንግስት አስረድተዋል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ከኢትዮጵያ -ቻይና ወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤቲ ዡ ጋር በጋራ በሚሰራባቸው ጉዳዮች የማዕቀፍ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።


ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ
አስተያየት መስጫ