“ጦርነቱ አብቅቷል” ትራምፕ

ምድብ : ዓለም አቀፍ | ንዑስ ምድቦች : ዓለም አቀፍ ዜናዎች የተለጠፈ ጊዜ 2025-12-03 08:13:45


“ጦርነቱ አብቅቷል” ትራምፕ

“ጦርነቱ አብቅቷል” ትራምፕ
*****************
ሀዋሳ፣ ጥቅምት 03፣ 2018 (ኤስቢሲ)
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛው ጦርነት አብቅቷል ፣ መካከለኛው ምሥራቅም ወደ መደበኛ ሁኔታው ይመለሳል" ሲሉ ተናገሩ ።
ትራምፕ ይሄንን ያሉት እስራኤልና ሐማስ ታጋቾችንና እስረኞችን ለመልቀቅ እየተጠባበቁ ባሉበት ወሳኝ ወቅት ነው።
ለሁለት አመታት የዘለቀውን የጋዛ ጦርነት ለመቋጨት በአሜሪካ በቀረበው የሰላም ስምምነት እቅድ መሰረት የመጀመሪያው ምዕራፍ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ተከትሎ ትራምፕ ወደ እስራኤል አቅንተዋል።
ትራምፕ በፕሬዚዳንት በአውሮፕላን (Air Force One) ላይ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንደሚጸና ያላቸውን እምነት ገልጸው፣ እንዲሁም የሰላም ቦርድ የተባለ ዓለም አቀፍ አካል በቅርቡ እንደሚቋቋም አስታውቀዋል።ፕሬዚዳንቱ የሰላም ስምምነቱ እንዲሳካ ላደረጉት ጥረት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን እና ቁልፍ ሚና የተጫወተችው ኳታርን አድንቀዋል።
በስምምነቱ የመጀመሪያ ምእራፍ መሰረት ሐማስ የቀሩትን ታጋቾች ለመልቀቅ የተዘጋጀ ሲሆን በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ እኩለ ቀን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል ። እስራኤልም በተመሳሳይ ወደ 2,000 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን እስረኞችን የምትለቅ ይሆናል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ እስራኤል እንደደረሱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በሀገሪቱ ፓርላማም ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው ።
ትራምፕ ከእስራኤል ጉብኝት በኋላ ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስቆም በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ግብፅ ሻርም ኤል ሼክ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ
አስተያየት መስጫ