ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በክልሉ እየተሰሩ ያሉ ሰራዎች ዘርፈ ብዙ እንደሆኑ የሲዳማ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለፁ።

ምድብ : ክልላዊ | ንዑስ ምድቦች : ክልላዊ ዜናዎች የተለጠፈ ጊዜ 2025-12-04 04:11:58

ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በክልሉ እየተሰሩ ያሉ ሰራዎች ዘርፈ ብዙ እንደሆኑ የሲዳማ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለፁ።

ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በክልሉ እየተሰሩ ያሉ ሰራዎች ዘርፈ ብዙ እንደሆኑ የሲዳማ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለፁ።
**********************
ሀዋሳ፣ ህዳር 24 ፣ 2018 (ኤሲቢሲ)
የሲዳማ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳማ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን በሁላ ወረዳና ዳራ ኦቶልቶ ወረዳ መሄር እርሻን ጎበኝተዋል።
የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ዜጎች ከድህነት ተላቀው ወደ ብልፅግና ከፍታ እንዲወጡ በሲዳማ ክልል ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ኘሬዝዳንቱ ገልፀዋል።
አክለውም ከዚህ ቀደም በነበረው ሁኔታገበሬው ውጤታማ እንዳልነበረ በመግለፅ አሁን ላይ ጠረጴዛማ እርከን የአሰራር ዘዴን በመጠቀም ምርታማነትን ማረጋገጥ መቻሉን ገልፀዋል።
በጉብኝቱ የተገኙት የሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምህሩ ሞኬ በበኩላቸው የመሬት አጠቃቀምን በማሻሻል በ2017-18 እንደ ክልል 160ሺ ሄክታር በላይ በመሄር እርሻ መሸፈኑን ገልፀዋል።
የሁላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሃንካርሶ ጎንሴ እንደሀገረ የተጀመረውን ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ በመግለፅ በዚህ አመት 49ታር በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 5445 ሄክታር መሬት በዘር እንደተሸፈነ ገልፀዋል።

ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ
አስተያየት መስጫ