ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የሠራተኛ ማኅበራት ንቅናቄ ለሚደግፋቸው መርሆዎች ከፍተኛ ዋጋ ትሰጣለች፡- አቶ አደም ፋራህ

ምድብ : ፖለቲካ | ንዑስ ምድቦች : ፖለቲካ የተለጠፈ ጊዜ 2025-12-05 01:30:40


ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የሠራተኛ ማኅበራት ንቅናቄ ለሚደግፋቸው መርሆዎች ከፍተኛ ዋጋ ትሰጣለች፡- አቶ አደም ፋራህ


ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የሠራተኛ ማኅበራት ንቅናቄ ለሚደግፋቸው መርሆዎች ከፍተኛ ዋጋ ትሰጣለች፡- አቶ አደም ፋራህ
************
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ የተካሄደውን 37ኛውን የዓለም የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ አስጀምረዋል፡፡
አቶ አደም ፋራህ፤ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሠራተኛ ማኅበራት ንቅናቄ የሚደግፋቸውን የሰላም፣ የዜጎች ክብር፣ የፍትህ፣ የዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ እና ዓለም አቀፍ ሕግጋትን የማክበር መርሆዎች ከፍተኛ ዋጋ ትሰጣለች ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።
በጉባዔው ላይ፣ ሠራተኞች እና አሰሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች እና መፍትሔዎች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ በሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብርና ቅንጅት የሚፈፀሙ ቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ አደም ፋራህ አመላክተዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው መንግሥት የሠራተኛ መብቶችን ለማስጠበቅ፣ እኩልነትንና ፍትሓዊነትን ለማስፈን፣ ማህበራዊ ጥበቃን ለማጠናከር፣ አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት እና የብልፅግና ጉዞን ለመፋጠን የአሰሪዎችን (የግል ሴክተሩን) ተሳትፎ በማሳደግና በሠራተኞች መብት አከባበር መካከል ሚዛን መጠበቅ ወሳኝ ነው ብሎ ያምናል ብለዋል።
በተያያዘም ተገቢ የሆኑ ቋሚ የሥራ እድሎችን ለማስፋፋትና የሠራተኞችን መብትና ጥቅም በተሻለ መልኩ ለማስከበር መንግሥታችን ለትምህርት ጥራት፣ ለቴክኖሎጂ፣ ለፈጠራ፣ ለኢንቨስትመንትና ምርታማነት እድገት በሰጠው ትኩረት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚ ተጠቃሚ አድርጓል ነው ያሉት።
ልማትን ይበልጥ ለማፋጠን፣ ፍትሐዊ ማኅበረሰብ ለመፍጠር እና ሰላማዊና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚያስችል መልኩ ተልዕኮውን ለመወጣት የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም በሀገራችን የሠራተኛ መብቶችን ለማስጠበቅ ላደረገው የማያቋርጥ ጥረት እና ይህ ዓለም አቀፍ ጉባዔ በሀገራችን እንዲዘጋጅ ለተጫወተው ከፍተኛ ሚና ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።
37ኛው የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ጉባዔም ስኬታማ እና እንግዶቹ በአዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ አስደሳች እንዲሆን አቶ አደም ፋራህ ተመኝተዋል።


ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ
አስተያየት መስጫ