በኮሪደር ልማቱ አዲስ መልክ የለበሰችው ሀዋሳ

በኮሪደር ልማቱ አዲስ መልክ የለበሰችው ሀዋሳ

የኮሪደር ልማት የከተሞችን ነባራዊ ገጽታ በመቀየር፣ የመሠረተ ልማት ትስስርን በማጠናከርና የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚተገበር ዘመናዊ የከተማ ፕላን አካል ነው።
በዚህ ረገድ በፍጥነትና በጥራት የተከናወነው የሀዋሳ የኮሪደር ልማት ለሌሎች ከተሞች በአርአያነት የሚጠቀስ ሆኗል።
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እንደገለጹት፤ አዲሱ የኮሪደር ልማት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት በቅቷል።
ለዚህ ስኬት የከተማው ነዋሪና መንግሥት ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባው፤ ልማቱ ነዋሪዎች በምሽት እንዲዝናኑ፣ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲስፋፋና የትራፊክ ፍሰቱ እንዲሳለጥ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስረድተዋል።
በከተማው በሁለተኛው ዙር 6.5 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ በአጠቃላይ 17.9 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ የእግረኛ መንገዶች ተገንብተዋል።
በተጨማሪም የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስና ጤናማ ትራንስፖርትን ለማበረታታት ምቹ የብስክሌት መንገዶች ተካተዋል። ይህም ቀደም ሲል እየጠፋ የነበረውን የብስክሌት እንቅስቃሴ መልሶ እንዲያንሰራራ አድርጎታል።
ልማቱ ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቀጥተኛ ድጋፍ ለሥራው መፋጠን ትልቅ ሚና እንደነበረው አቶ ጥራቱ አመልክተዋል።


አስተያየትዎን ያጋሩ
ቋንቋ ይቀይሩ
ፍለጋ
ወቅታዊ ዜናዎች
የስራ ማስታወቂያ
SBC
የፌስቡክ ገጽ
ዩቲዩብ